ቀጥታ፡

የህወሓት ተቃርኖ ከድብቅ ሰነዱ

በሚፍታህ አህመድ (ኢዜአ)

ህዝባዊ ወያኔ ሓርነት ትግራይ (ህወሓት) ከምስረታው ጀምሮ   በአስተሳሰብ አብሮ የማይሄዱ አባሎቹን ሲረሽን ለዓላማው ማስፈጸሚያ ከሚሆኑት ጋር ደግሞ ሲተባበር የነበረ ሴረኛና ጥቅምኛ ድርጅት ስለመሆኑ በርካታ ሰነዶች ያስረዳሉ፡፡ አሸባሪው ህወሓት “ኢህአዴግ” የሚል ጭምብል ለብሶ ኢትዮጵያን በ1983 ዓም በሀይልና በሴራ ከተረከባት ጊዜ ጀምሮ በርካቶችን ለሞት ዳርጓል፣ ቁጥራቸው ቀላል ያልሆኑ ዜጎችን ደግሞ ከቀያቸው አፈናቅሏል፤ አለያይቷል በጥቅሉ አገር በዝብዟል።  

ይህ የሽብር ቡድን ስልጣን ላይ በነበረበት ወቅት በሚፈጽማቸው ዘግናኝና ጨቋኝ ባህሪው  በህዝብ ተገፍቶ መቀሌ በመከተም ድሮ በድብቅ ሲያሰራጨው የነበረውን እኩይ ተግባር በግልጽ ሲያራምድ ቆይቶ በእኩይ ተግባሩ ጅምላ ጭፍጨፋ አካሄዷል፣ በርካቶችን አፈናቅሏል፣ ብዙዎችን አስለቅሳል፣ አገር አደጋ ውስጥ ጥሏል፡፡ አሸባሪው ህወሓት መቀሌ ከከተመ በኋላም እኔ “ከሞትኩ ሰርዶ አይብቀል” በሚለው ስግብግብ ባህሪው ድብቅ ሰነድ በማዘጋጀት በግብር ከሚመስሉት የውስጥ እና የውጭ ሀይሎች ጋር በመጣመር አገር የማፍረስ ተግባሩን በግልጽ ጀምሯል፡፡

በእርግጥ ህወሓት ከመነሻው ጀምሮ ሁለት አይነት ሰነድ በማዘጋጅት ህዝብን ማታለል የተካነበት ሰጣናዊ ምግባሩ ቢሆንም በዚህ "የትግል ልዩ ምዕራፍ እድገቶች እና የምከታችን ቀጣይ ስትራቴጂዎች፣ ስልቶች እና አቅጣጫዎች (ቁጥር - ሁለት) በጥብቅ የሚያዝ" በሚል የተዘጋጀው ድብቅ ሰነድ ከነማን ጋር በማበር እንዴት አገርን በማፍረስ ታላቋን ትግራይ መገንባት ግብን አድረጎ የተተነተነበት ሰነድ ነው፡፡

በድብቅ ባዘጋጀው ሰነድ   ላይ  እንደገለጸው  በፌደራል መንግስት ውስጥ ስልጣኑን በበላይነት በተቆጣጠረበት ዘመን  ከትግራይ ፍላጎት ውጭ የትግራይን ክልል ከተቀረው ኢትየጵያ ክልሎች በተለየ መንገድ ለመለውጥ አልሞ ይሰራ እንደነበር በይፋ አርጋግጧል፡፡ በሰነዱ ገጽ ስድስት ላይ"በ25 አመታት ውስጥ ትግራይን ትራንስፎርም ማድረግ አለብን የሚል ሀሳብ አንዱ መነሻው በሚኖረው ጊዜ እና ሂደት በአለም ደረጃ ትልልቅ ለውጦች መከሰታቸው/ መምጣታቸው ስለማይቀር የሚፈጠሩን እድሎች ለመጠቀም እና የሚያጋጥሙንን ከባድ ፈተናዎች በብቃት ለመመከትም ተስተካክለን ለመቆየት/ ለመጠበቅም ነው"  ሲል አስፍሯል፡፡ በዚህ ገለጻ ውስጥ በአለም የሚከሰቱ ለውጦችን  ለትግራይ ጥቅም ብቻ ማድረግ አለብን የሚል ግልጽ መልዕክት ያለው ነው፡፡ በቀጣይም ወደ ስልጣን በመመለስ የትግራይ ዘላቂ ልማት እንዴት መመለስ እንዳለበት በዚህ ሰነድ መግቢያ ላይ ሰነዱ የሚመለሳቸውን ይዘቶች በገለጹበት ክፍል ላይ በገልጽ ተቀምጦ ይገኟል፡፡ እንደሚታወቀው የትግራይ ህዝብ ከተቀረው ከኢትየጵያን ወንድም ህዝቦች ጋር በጋራ መልማትና ማደግ እንጅ ኢትዮጵያን በማደከም ትግራይን ማበልጽግ የሚል የራስ ወዳድነት  ባህል የሌለው ኩሩ ህዝብ ነው፡፡ ነገር ግን ከህዝብ ፍላጎት ውጭ ኢ- ፍትሃዊ በሆነ መልኩ የኢትዮጵያ ዕድገት ጥቅማችንን ይነካል የሚል ስጋት ከለባቸው ባዕዳን ጋር በማበር በኢትየጵያ ውድቅት ላይ   ትግራይን ለማበልጽግ በማሴራ ተግባር ውስጥ ለመግባት የባዕዳንን ፍላጎት እንደ አለመቀፍ ታላላቅ ለውጦች አድርጓ አስቀምጧል፡፡

ሌላው በዚህ ሰነድ ላይ የተገለጸው ድርጅቱ ከሌሎች መሰል አጋሮች ጋር በመስራት ዕቅዳችንን እናሳካለን የሚል ነው፡፡ በዚህም ኦነግ አሁን ለሁለት ተከፍሎ ሸኔ ከሚባለው አሸባሪ ድርጅት ጋር በመናበብ እሰራው ነው ሲል ቢገልጽም ህወሓት ስልጣን ላይ በነበረበት ወቅት ለይስሙላ በሚያካሂደ በምርጫ እንኳን እንዳይሳተፍ አሸባሪ ብሎ በመፈረጅ ከአገር እንዲወጡ አድርጎ እንደነበር የቅርብ ጊዜ ትውሰታ ነው፡፡

አሸባሪው ህወሓት በተቃርኖ ባህሪው ከስልጣኑ በህዝብ ተቃውሞ ከተባረረ በኃላ  የድርጅቱ ወደጅ፣ አፍቃሪ፣ደጋፊና ያለ እፍረት ዋነኛ ተቆርቋሪ  ሆኖ ብቅ ብሏል፡፡ በታሪክ እንደሚታወቀውም ህወሓት   ወደ ስልጣን  የወጣው ኦነግን መሰላል አድርጎ በሻብያ ተደገፎና ከፍተኛ ክህደት ፈጸሞ ነው፡፡ ስልጣኑንም በሚገባ ከተቆጧጠረ በኃላም አሁን ላይ እኔን ወደ ዳግም ስልጣን ለማምጣት ከፍተኛ ትግል እያደረጉ ነው ብሎ የሚመጸደቅባቸው አከባቢዎችን  የሃበት ምዝበራ የፈጸመባቸን መሆኑ የሚታወቅ ነው፡፡

በዚህ ድብቅ ስተራቴጂው እሱ በስልጣን በነበረበት ወቅ በኢ-መደበኛነት ተደራጅተው አሁን ለውጥ ለማምጣት ሲታገሉ የነበሩ አካላትን ስራ ዕጥ ሲላቸው አንዳንዴም ባስ ሲል ሰይጣን ብሎ ሲጠራቸው እንዳልነበር ዛሬ አገር ለማፍረስ ዕቅድን ፍላጎት  የሌላቸውን እነዚህ አደረጃጀቶችን በመጠቀም  አገር ለማፍረስ ይጠቅሙኛል በሚል አጋርነቱን እያሳየ ይገኛል፡፡

ይህ ድርጊቱ ደግሞ አሸባሪው ህወሓት አገር ለማፍረስ ከሚረዱት አካላት ጋር ከማበር እስከ ሲኦል መግባት የሚለው ባህሪያቸው በተቃርኖ የሚያሳይ ተግባር ነው፡፡

ለተቃርኖው ማሳያ ደግሞ በአንድ ውቅት የአሸባሪው  ቡድን አፈ ቃላጤ ጌታቸው ረዳ የኦሮሞ ወጣቶችን  “የሰይጣን መንጋ” በማለት እንዳላጣጣሉ ዛሬ ድግሞ በቅስቀሳ አታለው ወደ ስልጠን ለመመለስ የሚያስችላቸውን ጠንካራ ትግል እያደረገላቸው መሆኑን በሰነዱ ላይ በተደጋጋሚ ተገልጾ ይገኛል፡፡ የሚገርመው በኦሮሚያና በኦሮሞ ላይ ያ ሁሉ የፈጸሙት ግፍ እረስተውት እራሳቸውን  የቄሮ አፍቃሪ ለቄሮ ተቋርቃሪ ሆነው አይናቸውን በጨው አጥበው ብቅ ብለዋል፡፡

ወደ ስልጣን ለመመለስ ከፍተኛ ተስፋ ያደረገባቸውን እነዚህ አከባቢዎች በሚያሳዝን ሁኔታ ንጽሃኖች በጅምላ ያስጨረሰበት፣ የሽበር ወንጀል የፈጸመበት፣ የግለሰቦችና የአገር ሃብት ያወደመበት አሳዛኝ ታሪክ በሰበአዊ የሰው ልጆች ላይ የፈጸበት፣ የአገርን ልዓላዊነት አደጋ ላይ ለመጣል ከሚያሴሩ የውስጥ ባንዳዎችና ከወጭ ጠላቶች ጋር ቀጥተኛ ግንኙነት አንዳለው እራሱን በራሱ ያጋለጠበት ነው፡፡ ከዚህም በላይ ህወሓት ሰላማዊና  ሰላም በማስከበር ጠንከራ ድርጅት እንደሆ፣ ለዜጎች ደህንንትና መብት  መከበር  የሚተጋ መሆኑን ሰርክ ባገኘው አጋጣሚ ሲገልጹ የሚሰማ ቢሆንም እውነታው ግን በተገላብጦሽ በግጭት የተካነ፣ በንጹሃን ላይ በህብኡ ጭፍጨፋ የሚያካሂድ፣ በደም የተጨማለቀ አሸባሪ ድርጅት መሆኑን በግልጽ የገለጸበት ሰነድ ነው፡፡

በጥቅል ሰነዱ ባለፉት 30 አመታት በሲዳማ፣ በሱማሊያ፣አፋር፣ ጋንቤላ፣ ደቡብ፣አማራ ወዘተ ክሎሎች ላይ የፈጸመውን ብዝበዛና ከፍተኛ የሰበአዊ መብት ጥሰት ዘንግቶት ዛሬ የኢትዮጵያን ህዝብ በሃሰተኛ ፕሮፖጋንዳ አሳምኜ ወደ ስልጣን እመለሳለው የሚል ይዘት ያለው ላም አለኝ በሰማይ አይነት ምኞት የትንላቱን አሳፋሪ ተግባሩ ከዛሬ ምኞቱ ጋር በፍጹም የማይገጥም ሰነድ መሰነዱ አግራሞትን የሚፍጥር ነው፡፡

የኢትዮጵያ ዜና አገልግሎት
2015
ዓ.ም