"የዛሬ ጣይቱ እንሁን" በሚል መሪ ሃሳብ ሴት ሚኒስትሮች በደሴ ከተማ ለሚገኙ ተፈናቃዮች ድጋፍ አደረጉ - ኢዜአ አማርኛ
"የዛሬ ጣይቱ እንሁን" በሚል መሪ ሃሳብ ሴት ሚኒስትሮች በደሴ ከተማ ለሚገኙ ተፈናቃዮች ድጋፍ አደረጉ
መስከረም 09 ቀን 2014 (ኢዜአ) "የዛሬ ጣይቱ እንሁን" በሚል መሪ ሃሳብ ሴት ሚኒስትሮች በደሴ ከተማ ለሚገኙ ተፈናቃዮች ድጋፍ አደረጉ።
በአሸባሪው ህወሃት ወረራ ተፈናቅለው በደሴ ከተማ ሰኞ ገበያ 1ኛ ደረጃ ትምህርት ቤት ለተጠለሉ ዜጎች ምክትል አፈ-ጉባኤ ሽታየ ምናለን ጨምሮ ሴት ሚኒስትሮች፣ ከፍተኛ አመራሮችና ባለሃብቶች ምግብ እና ምግብ ነክ ያልሆኑ ቁሳቁሶች ድጋፍ አድርገዋል።
ከተደረገው ድጋፍ ውስጥ የእናቶችና ህፃናት ኃይል ሰጪ ምግብ ይገኝበታል።
የባህልና ቱሪዝም ሚኒስትሯ ዶክተር ሂሩት ካሳው፤ "በአሸባሪው ህወሃት ወረራ ሳቢያ የተፈናቀሉት ወገኖች አስቸኳይ ድጋፍ ይሻሉ" ብለዋል።
ለዚህም በውጭም ይሁን በአገር ውስጥ ያሉ ዜጎች ሁሉ ካላቸው እየቀነሱ ድጋፍ እንዲያደርጉ ጠይቀዋል።
ኢዜአ ያነጋገራቸው ተፈናቃዮች በበኩላቸው በአሁኑ ወቅት ህይወታቸው በአስቸጋሪ ሁኔታ ላይ የሚገኝ በመሆኑ ሁሉም ወገን ድጋፍና እገዛ እንዲያደርጉላቸው ጠይቀዋል።
የመንግስት አካላትና የሚመለከታቸው የረድኤት ድርጅቶችም እንዲያግዟቸው መልእክታቸውንም አስተላልፈዋል።