የሲቪል ማህበረሰብ ድርጅቶች አመራርና ሠራተኞች "የነጭ ፖስታ ጎርፍ ወደ ነጩ ቤተ - መንግስት" ዘመቻን ተቀላቀሉ - ኢዜአ አማርኛ
የሲቪል ማህበረሰብ ድርጅቶች አመራርና ሠራተኞች "የነጭ ፖስታ ጎርፍ ወደ ነጩ ቤተ - መንግስት" ዘመቻን ተቀላቀሉ
አዲስ አበባ መስከረም 7/2014 (ኢዜአ) የሲቪል ማህበረሰብ ድርጅቶችና የሲቪል ማህበረሰብ ድርጅቶች ኤጀንሲ አመራር እና ሠራተኞች "የነጭ ፖስታ ጎርፍ ወደ ነጩ ቤተ - መንግስት" ዘመቻን በይፋ መቀላቀላቸውን ገልጸዋል።
የኢትዮጵያን እውነታ ለመላው ዓለም ለማሳወቅ ዓላማ ያደረገው “የነጩ ፖስታ ጎርፍ ወደ ነጩ ቤተ-መንግስት” ንቅናቄ መጀመሩ ይታወቃል።
የሲቪል ማህበረሰብ ድርጅቶች ኤጀንሲ ምክትል ዳይሬክተር አቶ ፋሲካው ሞላ ኢትዮጵያውያን ሀገራቸው የገጠማትን በፈተና በድል ለመወጣት ከፍተኛ ርብርብ እያደረጉ ይገኛሉ ነው ያሉት።
አንዳንድ የውጭ ሀገራት በኢትዮጵያ የውስጥ ጉዳይ ላይ ጫና ለመፍጠር እያደረጉ ያሉትን ተፅእኖ የሲቪል ማህበረሰብ ድርጅቶች እንደማይቀበሉትም አንስተዋል።
በመሆኑም የሲቪል ማህበረሰብ ድርጅቶችና የሲቪል ማህበረሰብ ኤጀንሲ አመራርና ሰራተኞች "የነጭ ፖስታ ጎርፍ ወደ ነጩ ቤተ - መንግስት" ዘመቻን በይፋ ተቀላቅለዋል ብለዋል።
ምክትል ዳይሬክተሩ የተጀመረው ንቅናቄ በህዝቡ መካከል ያለውን አንድነት ይበልጥ እንደሚያጠናክረውም ተናግረዋል።
የኢትዮጵያ ሲቪል ማህበረሰብ ድርጅቶች ምክር ቤት ምክትል ፕሬዝዳንት አቶ አህመድ ሁሴን በበኩላቸው አንዳንድ የውጭ ሀገራት ኢትዮጵያ ላይ እያደረጉ ያለውን ጫና በአንድነት ልንቃወም ይገባል ብለዋል።
ሁሉም ዜጋ ኢትዮጵያ የያዘችውን እውነት ለዓለም አቀፉ ማህበረሰብ የማሳወቅ ኃላፊነት እንዳለበትም ነው የገለጹት።
የተለያዩ የህብረተሰብ ክፍሎች ”የነጭ ፖስታ ጎርፍ ወደ ነጩ ቤተ - መንግስት" ዘመቻን በይፋ በመቀላቀል የሀገራቸውን እውነት ለዓለም አቀፉ ማህበረሰብ በማሳወቅ ረገድ የበኩላችንን ሚና እየተወጡ ይገኛሉ።