ቀጥታ፡

አሸባሪውን የህወሓት ወራሪ ኃይል በአጭር ጊዜ በመቅበር ለሰሜን ወሎ ሕዝብ ድል ለማብሰር ዝግጁ ነን

አዲስ አበባ፣ መስከረም 7/2014 (ኢዜአ) የህወሓትን ወራሪ ኃይል በገባባቸው አካባቢዎች ሁሉ በአጭር ጊዜ በመቅበር ለሰሜን ወሎ ሕዝብ ድል ለማብሰር በዝግጅት ላይ እንደሚገኙ በወሎ ግንባር የተሰለፉ የጦር መኮንኖችና የሠራዊት አባላት ገለጹ።


የ13ኛ ክፍለ ጦር አንደኛ ሬጅመንት አዛዥ፤ አሸባሪው የህወሓት ቡድን በአጭር ጊዜ ለማጥፍት ሠራዊቱ በአስተማማኝ ዝግጁነት ላይ እንደሚገኝ ገልጸዋል።

ኢትዮጵያ ክብሯንና ማንነቷን አስጠብቃ እንድትቀጥል ሠራዊቱ ከውጊያ ግዳጅ ጎን ለጎን የአቅም ማጎልበቻ ስልጠና እየወሰደ እንደሚገኝ ተናግረዋል።

የ6ኛ ሞተራይዝድ ሬጅመንት አዛዥ ደግሞ "በግንባሩ ያለውን ወራሪ ኃይል በመደምሰስ ከምድረ ገጽ ለማጥፋት ሙሉ ዝግጁነት ላይ እንገኛለን" ብለዋል።

የሠራዊቱ አባላትም አሸባሪውን የህወሓት ቡድን ለማጥፋት ሙሉ የስነ-ልቦና ዝግጁነት እንዳላቸው ተናግረዋል።

ወጣቱ ትውልድ የአገር ፍቅርን በመላበስ ሉዓላዊነቷን ለማስጠበቅ ሠራዊቱን እንዲቀላቀልም የ13ኛ ክፍለ ጦር አንደኛ ሬጅመንት ምክትል አዛዥ ጥሪ አቅርበዋል።

የኢትዮጵያ ዜና አገልግሎት
2015
ዓ.ም