ቀጥታ፡

የወቅቱን የኢትዮጵያ እውነታ ለዓለም ማህበረሰብ ለማሳወቅ የተዘጋጀ መርሀ ግብር በጋምቤላ ተጀመረ

መስከረም 6/2014/ኤዜአ/ አሸባሪው ህወሓት እየፈጸመ ያለውን እኩይ ተግባርና የወቅቱን የኢትዮጵያ እውነታ ለዓለም ማህበረሰብ ለማሳወቅ የተዘጋጀ የሀሳብ ማሰባሰቢያ መርሃ ግብር ዛሬ በጋምቤላ ክልል በይፋ ተጀመረ።
መርሃ ግብሩን ያስጀመሩት የክልሉ ርዕሰ መስተዳድር አቶ ኡሞድ  ኡጁሉ ናቸው።

ርዕሰ መስተዳድሩ በወቅቱ እንዳሉት አሸባሪው  የህወሓሃት  ቡድን እየፈፀመ  ያለውን  እኩይ ተግባር  ለዓለም አቀፍ  ማህበረስብ  ለማስወቅ  ያለመ  መርሀ ግብር ተጀምሯል።

በተለይም አሜሪካንን ጨምሮ ምዕራባዊያን ሀገራት በኢትዮጵያ ላይ የያዙትን የተዛባ መረጃ ለማስተካከልና ሁኔታውን ለማሳየት ያለመ መርሃ ግብር መሆኑን ተናግረዋል።

መርሃ ግብሩ በክልሉ ወጣቶች ሊግ አስተባባሪነት የሚካሄድ መሆኑን አስታውቀዋል።

የክልሉ የወጣቶች  ሊግ ፕሬዝዳንት  ወጣት ሯች ጎች  በበኩሉ መርሀ ግብሩ  በክልሉ  ከዛሬ መስከረም 6  እስከ 15 ቀን 2014 ዓም  እንደሚካሄድ አመልክቷል።

እንደ ወጣት ሯች ገለጻ በመርሀ ግብሩ 50 ሺህ ሀሳቦች ይሰበሰባሉ።

የኢትዮጵያ ዜና አገልግሎት
2015
ዓ.ም