የቻይና የጠፈር ተመራማሪዎች በነገው ዕለት ወደ ምድር ይመለሳሉ፡፡ - ኢዜአ አማርኛ
የቻይና የጠፈር ተመራማሪዎች በነገው ዕለት ወደ ምድር ይመለሳሉ፡፡
አዲስ አበባ፣መስከረም 06/2014 (ኢዜአ) በቆይታቸው አዲስ ሪከርድ የሰበሩ አስራ ሁለት የቻይና የጠፈር ተመራማሪዎች በነገው ዕለት ወደ ምድር የሚመለሱ መሆኑን የቻይናው የሽንዦ ስፔስ ኢንጂነሪንግ አሳወቀ፡፡፡፡
ተማራማሪዎች ወደ ምድር የሚመለሱባት መንከራኩር ዛሬ ጠዋት ከህዋ ጣቢያ ተነስቷል፡፡
በመሬት ላይ ያሉ የቴክኒክ ሠራተኞች አስፋለጊውን የቅደመ ዝግጅት ስራ አጠናቀው ጠፍተኞችን በመጠባበቅ ላይ ናቸው፡፡
ጠፈርተኞቹ ከማዕከላዊ የህዋ ጣቢያ ወደ ምድር መረጃን መለዋወጥ የሚያስችል ቴክኖሎጂ ን መሰረት መጣላቸውን ሲጂቲኤን ዘግቧል፡፡
ተማራማሪዎቹ በጠፈር ጣቢያው ለ 90 ቀናት መቆየታቸው በቻይና ታሪክ የመጀመሪያ መሆኑ አዲስ ሪከርድን ነው ተብሏል።
ቻይና በ400 ኪሎ ሜትር ከፍታ ላይ ምድርን የሚዞረው የጠፈር ጣቢያ በመግንባታ ላይ እንደምትገኝ ዘገባው አስታውሷል፡፡
የጠፈር ጣቢያውን ለማጠናቀቅ ስምንት ተጨማሪ ተልእኮዎች በዝግጅት ላይ መሆናቸውን ሲ ጂ ቲ ኤን ዘግቧል።