ወሰን ተሸግሮ የመጣው ሸብርተኞው የህውሃት ቡድን ባደረስነበት ከባድ ምት የጥፋት ዓላማው በማክሸፍ ለሌላ ድል ተነሳስተናል - ኢዜአ አማርኛ
ወሰን ተሸግሮ የመጣው ሸብርተኞው የህውሃት ቡድን ባደረስነበት ከባድ ምት የጥፋት ዓላማው በማክሸፍ ለሌላ ድል ተነሳስተናል
መስከረም 05/2013 (ኢዜአ) የአፋር ክልል ወሰን ተሸግሮ የመጣውን አሸባሪውን የህውሃት ቡድን ባደረስንበት ከባድ ምት የጥፋት ዓላማውን በማክሸፍ በከፍተኛ የሀገር ፍቅር ስሜት ለሌላ ድል ተነሳስተናል ሲሉ የሠራዊቱ አባላት ተናገሩ።
በአፋር ክልል ጭፍራ ግንባር በግዳጅ ላይ የሚገኙ የምስራቅ ዕዝ ሠራዊት አባላትን የማነቃቃትና ለቀጣይ ግዳጅ የማነሣሣት መርሀ ግብር ተካሄዷል፡፡
መርሀ ግብርሩ በቀጣይ ላለው ግዳጅ እንዲዘጋጁና ለበለጠ ድል እንዳነሣሣቸው የሰራዊቱ አባላት ገልጸዋል፡፡
ካሁን በኋላ የሸብር ቡድኑ ፈፅሞ የኢትዮጵያ ህዝብ የደህንነት ስጋት ሊሆን አይችልም፤ እኛ እያለን የቡድኑ ሀገር የማፍረስ ተግባርም ሊሣካ አይችልም ብለዋል፡፡
መጀመሪያ ወደ ግንባሩ ስንገባ የነበረው ከባድ ውጊ በላቀ የሀገር ፍቅር ስሜት በመግፋት የሽብር ቡድኑ አባላት አብዛኛዎቹ አልቀዋል ነው ያሉት የሠራዊቱ አባላት።
ተገደውም በፈቃደኝነት ከሸብር ቡድኑ ጎን የተላለፉ የትግራይ ክልል ወጣቶች ቡድኑ ለማይሣካው የስልጣን ጥማት ያልተገባ መስዋዕትነተ መክፈል እንደሌለባቸው የሠራዊቱ አባላት አመልክተዋል።
በየአቅጣጫው ለሰራዊት እየተደረገ ያለው ድጋፍና የህዝብ አጋርነት እናመስግናለን ብለዋል፡፡
ንጹሀንን በመግደልና እንዲፈናቀሉ በማድረግ ለከፍ ችግር ተጋላጭ አድርጎ የነበረው ሸብርተኞው ህውሃት ቡድን ባደረስንበት ከባድ ምት የጥፋት ዓላማውን በመክሸፍ ለሌላ ድል መነሳሳታቸውን ያስታወቁት።