ቀጥታ፡

በአደንዛዥ እጽ ዝውውር የተጠረጠሩ ግለሰቦች ተያዙ

ነገሌ፣ መስከረም 04 ቀን 2014 (ኢዜአ) በነገሌ ከተማ በአደንዛዥ እጽ ዝውውር የተጠረጠሩ ሶስት ግለሰቦች በቁጥጥር ስር መዋላቸውን ፖሊስ አስታወቀ።

የጉጂ ዞን ፖሊስ መምሪያ ወንጀል መከላከል ምክትል ዳይሬክተር ዋና ሳጂን ጉተማ ሳፋይ ለኢዜአ እንደገለጹት፤ ከትናንት በስቲያ በከተማው በአንድ ግለሰብ መኖሪያ ቤት በተደረገ ፍተሻ 20 ኪሎ ግራም የሚመዝን ካሳቢስ የተሰኘ አደንዛዥ እጽ ተገኝቷል።

ከተገኘው ካናቢስ ጋር ተያይዞ በአደንዛዥ እጽ ዝውውር የተጠረጠሩ ሶስት ግለሰቦች በቁጥጥር ስር ውለው በፖሊስ ምርመራ እየተካሄደ መሆኑን ተናግረዋል።

አደንዛዥ እጹ ከሻሸመኔ ከተማ ኩየራ አካባቢ ተጓጉዞ ለአሸባሪው ሸኔ እንዲደርስ የተዘጋጀ ስለመሆኑ አመላካች መረጃዎች መገኘታቸውን ዋና ሳጅን ጉተማ አስታውቀዋል።

የኢትዮጵያ ዜና አገልግሎት
2015
ዓ.ም