ሰሜን ኮሪያ አዲስ የረዥም ርቀት ተወንጫፊ ሚሳኤል ሙከራ አደረገች - ኢዜአ አማርኛ
ሰሜን ኮሪያ አዲስ የረዥም ርቀት ተወንጫፊ ሚሳኤል ሙከራ አደረገች
መስከረም 3፤2014(ኢዜአ) ሰሜን ኮሪያ አዲስ የረዥም ርቀት ተወንጫፊ የመርከብ ላይ ሚሳኤል መሞከሯን አስታውቃለች።
ሰሜን ኮሪያ ያስወነጨፈቻቸው ሚሳዔሎች እስከ 1 ሺህ 500 ኪሎ ሜትር ርቀት የመምዘግዘግ አቅም እንዳላቸው ቢቢሲ ዘግቧል፡፡
ሰሜን ኮሪያ ሙከራ ላይ ያዋለችው ሚሳዔል በርካታ የጃፓን ስፍራዎችን መምታት የሚችሉ ናቸው ተብሏል፡፡
የአሜሪካው ወታደራዊ መስሪያ ቤት ድርጊቱን ''የአለም አቀፍ ማህበረሰብ ስጋት''ሲለው ጃፓን በበኩሏ ጉዳዩ "ትልቅ ትኩረት የሚሻ" ነው ብለዋለች፡፡