ቀጥታ፡

አቶ ርስቱ ይርዳው በአሸባሪው ህወሓት የተፈናቀሉ ዜጎችን ለመደገፍና ለመከላከያ ሠራዊት ያላቸውን አጋርነት ለማረጋገጥ ባህርዳር ገቡ

መስከረም 02 ቀን 2014 (ኢዜአ) የደቡብ ክልል ምክትል ርእሰ መሥተዳድር ርስቱ ይርዳው በአሸባሪው የህወሓት የተፈናቀሉ ዜጎችን ለመደገፍና ለመከላከያ ሠራዊት ያላቸውን አጋርነት ለማረጋገጥ ባሕር ዳር ገብተዋል።

ምክትል ርእሰ መሥተዳድሩ በአሸባሪው የህወሓት ወራሪ ኀይል ጥቃትና ዝርፊያ የተፈናቀሉ ዜጎችን ለመደገፍና የሽብር ቡድኑን እየተፋለመ ላለው የሀገር መከላከያ ሠራዊት ያላቸውን ደጀንነት ለማረጋገጥ ነው የተገኙት።

የአማራ ክልል ርእሰ መሥተዳድር አገኘሁ ተሻገርን ጨምሮ የክልሉ ከፍተኛ የሥራ ኀላፊዎች ባሕር ዳር ደጃዝማች በላይ ዘለቀ ዓለም አቀፍ አየር ማረፊያ በመገኘት አቀባበል አድርገውላቸዋል።

አሸባሪውና ዘራፊው የትህነግ ወራሪ ኀይል በአማራና በአፋር ክልል ባደረገው ወረራ በመቶ ሺዎች የሚቆጠሩ ዜጎች ተፈናቅለዋል፤በሚሊዮን የሚቆጠሩ ዜጎችም ለከፋ ችግር እየተጋለጡ ነው።

ኢትዮጵያዊያንም የሽብር ቡድኑን ሀገር የማፍረስ ተግባር በመመከትና ለተጎዱ ዜጎች ድጋፍ በማድረግ አጋርነታቸውን እያሳዩ ነው ።

የሲዳማ ክልል ርዕሰ መስተዳደር አቶ ደስታ ሌዳሞ በአሸባሪው የህወሓት ቡድን የተገዱ ወገኖችን ለመደገፍና የክልሉ መንግስትና ህዝብ ያለውን አጋርነት ለማረጋገጥ ባሳለፍነው ሳምንት ባህርዳር መሄዳቸውና 10 ሚሊዮን ብር ድጋፍ ማድረጋቸው ይታወሳል።

የኢትዮጵያ ዜና አገልግሎት
2015
ዓ.ም