ጀግናው የመከላከያ ሰራዊታችን ጦርነቱን በአጭር ጊዜ አጠናቆ ወደ ልማት እንደምንመለስ ባለሙሉ ተስፋ ነኝ ­- ምክትል ከንቲባ አዳነች አቤቤ

76

መስከረም 01 ቀን 2014 (ኢዜአ) “ጀግናው የመከላከያ ሰራዊታችን ጦርነቱን በአጭር ጊዜ አጠናቆ ወደ ልማት እንደምንመለስ ባለሙሉ ተስፋ ነኝ” ሲሉ የአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር ምክትል ከንቲባ አዳነች አቤቤ ገለጹ።

የደቡብ ወሎ ዞን በዓልን ከጀግናው የመከላከያ ሰራዊት ጋር ለማክበር ያዘጋጀው የአዲስ ዓመት የበዓል ፕሮግራም ላይ ምክትል ከንቲባዋን ጨምሮ ከፍተኛ የመንግስት የስራ ሃላፊዎች ተገኝተው በግንባር እየተፋለመ የሚገኘውን ሰራዊት አበረታተዋል።

በፕሮግራሙ ላይ የታደሙት ምክትል ከንቲባ አዳነች አቤቤ እንዳሉት፤ በዓሉን ግንባር ላይ  ከሰራዊቱ ጋር ማክበር ትልቅ የደስታ ስሜትና ኩራት ይፈጥራል።

የአሸባሪውን ህወሃት ወረራ በመመከት ኢትዮጵያን ለማዳን የዘመቱ ጀግኖች ድል እያስመዘገቡ መሆኑን ገልጸው፤ “አዲሱ ዓመት የሽብር ቡድኑ በአጭር ጊዜ ተደምስሶ ፊታችንን ወደ ልማት የምናዞርበት ይሆናል” ብለዋል።

ለመከላከያ ሰራዊቱና ለመላው የጸጥታ ሀይሎች በአዲስ አበባ ህዝብ ስም የ’እንኳን አደረሳችሁ’ ሲሉ የመልካም ምኞት መግለጫ መልዕክት አስተላልፈዋል።

የኢትዮጵያ ዜና አገልግሎት
2015
ዓ.ም