በአዋሽአርባ ማሰልጠኛ መሰረታዊ ውትድርና የሰለጠኑ ወታደሮች ተመረቁ - ኢዜአ አማርኛ
በአዋሽአርባ ማሰልጠኛ መሰረታዊ ውትድርና የሰለጠኑ ወታደሮች ተመረቁ
ዻጉሜን 04 ቀን 2013 (ኢዜአ) በአዋሽአርባ ውጊያ ቴክኒክ ትምህርት ቤት መሰረታዊ ውትድርና ያሰለጠናቸውን ወታደሮችን አስመረቀ።
ኢዜአ ያነጋገራቸው ተመራቂ ወታደሮች በቆይታቸው አስተማማኝ ወታደራዊ ስልጠና ማግኘታቸውን ተናግረዋል።በዚህም ኢትዮጵያን ለማፍረስ የሚሰሩ የውጭ ሃይሎችንና የውስጥ ከሃዲዎችን ለመመከት ዝግጁ ነን ሲሉ አረጋግጠዋል።
ኢትዮጵያን አፈርሳለሁ ብሎ የተነሳውን አሸባሪ የህውሃት ቡድን እስከ ወዲያኛው እንደመስሰዋለን ብለዋል።በምርቃት ስነ ስርአቱ ላይ የምድር ኃይል ምክትል አዛዥ የሰው ሃብት ልማት ሜጀር ጀኔራል እንዳልካቸው ወልደኪዳንን ጨምሮ ሌሎች ከፍተኛ የጦር መኮንኖች እንዲሁም ከፍተኛ የመንግስት የስራ ኃላፊዎች ተገኝተዋል።