ለአዲስ አመት የስጋ ውጤቶችን በጥራትና በተመጣጠነ ዋጋ ለማድረስ ዝግጅት መደረጉን ቄራዎች ድርጅት ገለጸ - ኢዜአ አማርኛ
ለአዲስ አመት የስጋ ውጤቶችን በጥራትና በተመጣጠነ ዋጋ ለማድረስ ዝግጅት መደረጉን ቄራዎች ድርጅት ገለጸ

አዲስ አበባ ዻጉሜን 3/ 2013 (ኢዜአ) ለአዲስ አመት የስጋ ውጤቶችን በጥራትና በተመጣጠነ ዋጋ ለማድረስ ዝግጅት መደረጉን የአዲስ አበባ ቄራዎች ድርጅት ገለጸ።
የድርጅቱ የኢንፎርሜሽንና ህዝብ ግንኙነት ሃላፊ አቶ አታክልቲ ገብረሚካኤል፤ ለ2014 አዲስ አመት በእርድ አቅርቦት ድርጅቱ ያደረገውን ዝግጅት በተመለከተ ለመገናኛ ብዙሃን መግለጫ ሰጥተዋል።
በመሆኑም ድርጅቱ ለ2014 አዲስ ዓመት ከ2 ሺህ 500 በላይ የዳልጋ ከብት እና ከ1 ሺ 500 በላይ በግና ፍየሎችን ለተጠቃሚዎች ለማቅረብ መዘጋጀቱን ተናግረዋል።
ለህብረተሰቡ ስጋውን ተደራሽ ለማድረግ 40 ዘመናዊ የቄራ ተሽከርካሪዎች መዘጋጀታቸውን ጠቁመዋል።
ለበዓሉ ህብረተሰቡ ከንጋቱ 11 ሰአት ጀምሮ ወደ ድርጅቱ በሬ ወይም በግና ፍየል በማምጣት ከ30 እስከ 40 ደቂቃ ባለ ጊዜ አሳርዶ መውሰድ ይችላል ብለዋል።
ለቅርጫ የተዘጋጁም ካሉ በሬውን አምጥተው በማስመርመር የእርድ አገልግሎት ማግኘት ይችላሉ ነው ያሉት።
ከእርድ በኋላ ድርጅቱ የሚፈለግበት ቦታ ድረስ የትራንስፖርት አገልግሎት እንደሚያቀርብም ገልጸዋል።
በዋናው መስሪያ ቤት እና አቃቂ በሚገኘው ቅርንጫፍ ቢሮ በሚገኙ ሱቆች በኪሎ የበግ ስጋ 210 ብር እንዲሁም የበሬ ስጋ በ285 ብር መግዛት እንደሚችሉም ጠቁመዋል።
ለአዲስ አመት የስጋ ውጤቶችን በጥራትና በተመጣጠነ ዋጋ ለማድረስ ዝግጅት መደረጉንም ሃላፊው ተናግረዋል።
ከዚህ ውጭ ጤንነቱ ያልተረጋገጠ እና ንፅህናው ያልተጠበቀ ስጋ በመጠቀም ማህበረሰቡ ኮሮናን ጨምሮ ለተለያዩ በሽታዎች እንዳይጋለጥ አቶ አታክልቲ አሳስበዋል። አነደ
የአዲስ አበባ ቄራዎች ደርጅት በቀን በአማካይ 3 ሺህ 500 ሰንጋዎችን በማረድ ለተጠቃሚዎች የማቅረብ አቅም አለው ብለዋል።
ከህገ ወጥ እርድ ጋር በተላፊው በቅርቡ በተደረገ ጥናት ከተማ አስተዳደሩ በህገ-ወጥ ሳቢያ እርድ ከ1 ነጥብ 2 ቢሊየን ብር በላይ እንደታውቋል።ሰዋል።