መከላከያ ሰራዊትና ሌሎችም የፀጥታ ሃይሎች አሻባሪውን ህወሃት በመፋለም የፈፀሙት ተጋድሎ የሚደነቅ ነው - ኢዜአ አማርኛ
መከላከያ ሰራዊትና ሌሎችም የፀጥታ ሃይሎች አሻባሪውን ህወሃት በመፋለም የፈፀሙት ተጋድሎ የሚደነቅ ነው
ጳጉሜን 2/2013 (ኢዜአ) በማይጠብሪ ግንባር መከላከያ ሰራዊትና ሌሎችም የፀጥታ ሃይሎች አሻባሪውን ህወሃት በመፋለም የፈፀሙት ተጋድሎ የሚደነቅ መሆኑን የምዕራብ ዕዝ የሙዚቃ እና ቴአትር ቡድን አባለት ገለጹ።
የምዕራብ ዕዝ የሙዚቃና ቴአትር ቡድን በማይጠብሪ ግንባር በመገኘት የጥበብ ስራቸውን ለሰራዊቱ አቅርበዋል።
በዕዙ የሙዚቃና ቴአትር አስተባባሪ ሻለቃ ታዘበው ንጋቱ፤ ሰራዊቱ ድል ባደረገበት ማይጠብሪ ግንባር ተገኝተን ከሰራዊቱ ጋር በማሳለፋችን ተደስተናል ብለዋል።
በማይጠብሪ ግንባር መከላከያ ሰራዊትና ሌሎችም የፀጥታ ሃይሎች አሻባሪውን ህወሃት በመመከት የፈፀሙት ተጋድሎ ታሪክ የማይዘነጋውና አስደናቂ ጀግንነት መሆኑን ተናግረዋል።
የሰራዊቱ ድል አድራጊነት ይበልጥ እንዲጠናከር በጥበብ ስራዎቻቸን ለማነቃቃት በስፍራው ተገኝተናል ብለዋል።
በቡድኑ የሳክስፎን ተጫዋች ሃምሳ አለቃ እያሱ ንብረት፤ ከዚህ በፊት በአሸባሪው የህወሃት ቡድን ተንኮል እና ሴራ ከሰራዊቱ አባልነት መውጣታቸውን ተናግረው መንግስት ያቀረበውን ጥሪ በመቀበል ዳግም ሰራዊቱን መቀላቀላቸውን ተናግረዋል።
በግንባር በመገኘት ስራዊቱን በሙያዬ ማገዝ በመቻለ እጅግ ደስተኛ ነኝ ብለዋል።
“በአገር ላይ ክህደት የፈፀመ ሃይል ላይ የአገር መከላከያ ሰራዊት የአንበሳ ክንዱን ሲያሳርፍ ማየት እጅግ የሚያስደስት ነው" ሲሉም ገልጸዋል።
የጥበብ ስራችንን ግንባር ድረስ ተገኝተን ማቅረባችን ሰራዊቱ የበለጠ ወኔ ታጥቆ አሸባሪውን የህውሃት ቡድን በአጭር ጊዜ እንዲደመስስ ያደርገዋል ያሉት ደግሞ ድምፃይ ሻአለቃ ባሻ ኦላና ናቸው።
አሸባሪው ቡድን እስኪጠፋ ድረስ ሁሉም በሙያዊ የትም፣ መቼም በምንም ሊዘምት ይገባዋል ብለዋል።