'ኢትዮጵያዊነት' በኪነ ጥበብ ባለሙያዎች አንደበት - ኢዜአ አማርኛ
'ኢትዮጵያዊነት' በኪነ ጥበብ ባለሙያዎች አንደበት
ጷጉሜን 1/2013 (ኢዜአ) 'ኢትዮጵያዊነት' በኪነ ጥበብ ባለሙያዎች አንደበት
ጳጉሜን 1 የኢትዮጵያዊነትን ቀን "ለኢትዮጵያ ክብር እቆማለሁ፤ እዘምራለሁ'' በሚል መሪ ሃሳብ በተለያዩ ዝግጅቶች ሲዘከር ውሏል።
የኢትዮጵያዊያን የማስተሳሰሪያ ማንነት የሆነውን 'ኢትዮጵያዊነት' ኢትዮጵያዊያን በተለያዩ አግባብ ይገልጹታል።
ኢትዮያዊነትን እንደት ይገልጹታል ሲል ኢዜአ የተለያዩ የኪነ ጥበብ ባለሙያዎችን ያነጋገረ ሲሆን በርካቶቹ "ኢትዮጽያዊነትን በቀላሉ መግለፅ አንችልም ጥልቅ ነው" ብለዋል።
የፈንድቃ ባህል ማዕከል መስራችና ባለቤት አርቲስት መላኩ በላይ የጳጉሜን ወር የኢትዮጵያ አንዷ መለያና መገለጫ በመሆኗ በተለያዩ ዝግጅቶች መታሰቡ የሚደነቅ ነው ብሏል።
ኢትዮጵያ የዘመን አቆጣጥር፣ ፊደል፣ ቀለምና ሽታ እንዳላት በመግለጽ፤ በዚህ ወር መከበሩም ያስደስታል ይላል።
"ኢትዮጵያዊንትን ለመግለጽ ቃላት ያጥረኛል፤ ስኖር ኢትዮጵያዊ በመሆኔ ኩራት ይሰማኛል፤ ሁሌም ኢትዮጵያን አስቤ ነው የምኖረው" ብሏል።
ኢትዮጵያዊነትን "ከሃይማኖቴ ላይቼ አላየውም" ሲልም ተናግሯል።
ጋዜጠኛና ደራሲ የምወድሽ በቀለ በበኩሏ ኢትዮጵያ ሁለንተናችን ኢትዮጵያዊነት ኩራታችን በማለት ገልፃለች።
አርቲስት ደሳለኝ አሳምነው በበኩሉ ኢትዮጵያዊነት መፋቀር፣ መተሳሰብ፣ አንድነትና መከባበር በሚሉ ቃላት ይገልጻል።
'አሁን አሁን ከኢትዮጵያዊነት መገለጫ እሴቶች አጉድለናል' የሚለው አርቲስቱ የጎደሉን እሴቶች ተሟልተው ሙሉ ኢትዮጵያዊነት ማንነታችን ይመለሳል ብሏል።
በህጻናትና ወጣቶች ቴአትር ቤት ታዳጊዋ የባህል ተወዛዋዣ ቤተልሄም እስራኤል፤ ኢትዮጵያዊነት ፍቀህ የማጨርሰው፤ በትንሽ ቃላት የማይገለጽ ትልቅ ስጦታ መሆኑን ትናገራለች።
በ13 ወር ፀጋዋ ኢትዮጵያ የወርኃ ጳጉሜን 5 ቀናቶች የኢትዮጵያዊነት፣ የአገልጋይነት፣ የመልካምነት፣ የጀግንነት፣ የድል ቃል ኪዳን ብስራት በሚል ተሰይሞ እየተዘከረ ይገኛል።