የኢትዮጵያዊነት ቀን በአዲስ አበባ በተለያዩ ዝግጅቶች እየተከበረ ነው - ኢዜአ አማርኛ
የኢትዮጵያዊነት ቀን በአዲስ አበባ በተለያዩ ዝግጅቶች እየተከበረ ነው
አዲስ አበባ (ኢዜአ) ጷግሜ 1/2013 የኢትዮጵያዊነት ቀን በአዲስ አበባ መስቀል አደባባይ በተለያዩ ዝግጅቶች እየተከበረ ነው።
ጳጉሜን-1 የኢትዮጵያዊነት ቀን ''ለኢትዮጵያ ክብር እቆማለሁ፤ እዘምራለሁ'' በሚል መሪ ሃሳብ በአዲስ አበባ መስቀል አደባባይ በተለያዩ ዝግጅቶች እየተከበረ ነው።
በመርሃ ግበሩ ላይ የጠቅላይ ፍርድ ቤት ፕሬዚደንት ማአዛ አሸናፊ፣ የአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር ምክትል ከንቲባ አዳነች አቤቤ እና የአገር መከላከያ ሰራዊት ከፍተኛ መኮነኖች እና በርካታ የመዲናዋ ነዋሪዎች ታድመዋል።
የጳጉሜን አምስቱም ቀናት በአዲስ አበባ “አዲስ አበባ የኢትዮጵያ የድል ነፀብራቅ” የሚል መሪ ሃሳብ ይዞ ይከበራል።
በዚሁ መሰረት በጳጉሜን 1 በኢትዮጵያዊነት ላይ አተኩሮ በተለያዩ ዝግጅቶች በመከበር ላይ ይገኛል።
በቀጣዮቹ ተከታታይ ቀናት ጳጉሜን 2 የአገልጋይነት ቀን፣ ጳጉሜን 3 የመልካምነት ቀን፣ ጳጉሜን 4 የጀግንነት ቀን፣ ጳጉሜን 5 የድል ቃል ኪዳን ብስራት ቀን ሆነው በተለያዩ ዝግጅቶች እንደሚከበሩ የወጣው መርሃ ግብር ያመለክታል።
በነገው እልት ጳጉሜን 2 ለትራንስፖርት አገልግሎት ተጠቃሚዎች የተቀላጠፈ አገልግሎት በመስጠት የማህበረሰበ አገልጋይነት የሚገለፅበት ቀን ይሆናል።