ለአገር መከላከያ ሰራዊታችን ድጋፍና አጋርነትን ለመግለፅ የሩጫና የእግር ጉዞ ተደረገ - ኢዜአ አማርኛ
ለአገር መከላከያ ሰራዊታችን ድጋፍና አጋርነትን ለመግለፅ የሩጫና የእግር ጉዞ ተደረገ
ነሐሴ 30/ 2013 (ኢዜአ) እኔም ለአገሬ ወታደር ነኝ፤ ኢትዮጵያን ለማዳን እዘምታለሁ፤ የትም፣ መቼም፣ በምንም በሚል መሪ ቃል ዛሬ የሩጫና የእግር ጉዞ በአዲስ አበባ ተደረገ፡፡
5 ኪሎ ሜትርን የሚሸፍን የሩጫና የእግር ጉዞው የተካሄደው መነሻውንና መድረሻውን መስቀል አደባባይ አድርጎ ነው ።
አትሌቲክስ ፌዴሬሽ ከኢፌዲሪ ስፖርት ኮሚሽን ጋር በመተባበር ዛሬ ከንጋቱ 12 : 30 ጀምሮ በተደረገው መርሃ ግብር የሚኒስትር መስሪያ ቤቶች፣ ተጠሪ ተቋማትና የስፖርት ማህበራትና የከተማው ነዋሪዎች ተሳትፈዋል።
በአራት የእድሜ ምድብ በተደረገ የ5ኪሜ የጎዳና ውድድር ከ40 ዓመት በታች ወንዶች ሰለሞን በንቲ ከመከላከያ፣ ከ30 ዓመት በታች ሴቶች በፀሎት ስብሃት ከባህልና ቱሪዝም፣ ከ40 ዓመት በላይ ወንዶች ደበበ ወ/ሰንበት ከፌዴራል ማረሚያ፣ ከ30ዓመት በላይ ሴቶች ኩሪ መገርሳ ከፌደራል ማረሚያ አሸናፊ መሆናቸውን ከአትሌቲክስ ፌደሬሽን ያገኘነው መረጃ ያመላክታል፡፡