ተፎካካሪ የፖለቲካ ፖርቲዎች በወቅታዊ አገራዊ ጉዳይ ላይ እየመከሩ ነው - ኢዜአ አማርኛ
ተፎካካሪ የፖለቲካ ፖርቲዎች በወቅታዊ አገራዊ ጉዳይ ላይ እየመከሩ ነው

አዲስ አበባ፣ ነሀሴ 29/2013 ( ኢዜአ) ተፎካካሪ የፖለቲካ ፖርቲዎች በወቅታዊ አገራዊ ጉዳይ ላይ እየመከሩ ነው።
አዲስ አበባ ውስጥ እየተካሄደ ባለው ምክክር የብልጽግና ፓርቲ ስራ አስፈፃሚ አባል አቶ ተስፋየ በልጅጌ፣ አቶ ዛዲግ አብርሃ ጨምሮ ሌሎች የፓለቲካ ፖርቲ አመራር አባላትና የፓርቲዎች የጋራ ምክር ቤት አመራር አባላት እየተሳተፉ ናቸው።
አሸባሪው ህወሃት "እኔ ካልመራሁ ይቺ አገር መቀጠል የለባትም" በማለት ከአሸባሪው ሸኔ ጋር ስምምነት ፈጥሮ ጦርነት መክፈቱ ተነስቷል።
የብልጽግና ፓርቲ ስራ አስፈፃሚ አባል አቶ ተስፋየ በልጅጌ እንደተናገሩት፣ የአገርን ህልውና ለመታደግ በጋራ መስራት እንደሚገባ ገልጸዋል።
ምክክሩም አገርን ከተከፈተባት አደጋ ለመታደግ አቅም እንደሚፈጥር ነው ያመለከቱት።
ኢትዮጵያ በአሁኑ ወቅት ምጣኔ ሃብታዊ አሻጥር ጨምሮ የውጭ ጠላቶችና የውስጥ ባንዳዎች ቅንጅት በመፍጠር ዓይነተ ብዙ ጦርነት እንደከፈቱባት ገልጸዋል።
የአገራቱን ወቅታዊ ሁኔታ በሚመክረው የተፎካካሪ የፖለቲካ ፓርቲዎች ምክክር ላይ የፖርቲ አመራር አባላት ታድመዋል።