ቀጥታ፡

አሸባሪው ህወሓትን ለህዝብ ስጋት በማይሆን መልኩ ለመደምሰስ የድርሻችንን እንወጣለን

ሻሻመኔ፣ ነሃሴ 27/203 (ኢዜአ) አሸባሪው ህወሓት ዳግም ለህዝብ ስጋት በማይሆን መልኩ ለመደምስ  ዝግጁ ነን ይላሉ የምዕራብ አርሲ ዞን አስተዳደር መንግስት ሰራተኞች።
የመንግስት ሰራተኞች በወቅታዊ ሀገራዊ ጉዳይ ላይ ባደረጉት ወይይት ከወር ደሞዛቸው 10 ሚሊዮን ብር ለመከላከያ ስራዊት ለመደገፍ ቃል ገብተዋል።
ከውይይቱ ተሳታፊዎች መካከል የሻሸመኔ ከተማ ነዋሪ ወይዘሮ አራቤ ኛጉሌ እንደገለጹት ህወሓት አገር ለማፍረስ ከውጭ ሀይሎች ጋር በቅንጅት ተባባሪ በመሆን ይሰራል፤

ይህ ቡድን እድሜ ልኩን በኢትዮጵያ ህዝብ ላይ የሰራው በደልና ግፍ አልበቃው ብሎ ዛሬም ለሰዎች ሞት፣ መፈናቀልና ለንብረት ውድመት ምክንያት በመሆኑ አንድ ሆነን ልንደመስሰው ይገባል" ብለዋል።

ለሰራዊቱ የአንድ ወር ደሞዛቸውን ድጋፍ ለማድረግ መወሰናቸውን ከማረጋገጣቸውም በላይ በሴቶች አደረጃጀት ተደራጅተውም ለሰራዊቱ ስንቅ እያዘጋጁ መሆናቸውንም ተናግረዋል፡፡
ሌላው የዞኑ ገቢዎች ጽህፈት ቤት ሰራተኛ አቶ ነጋሶ ሁሉፌ በበኩላቸው ከመከላከያና ፀጥታ አባላት ጎን ተሰልፈን አሸባሪውን ቡድን ዳግም ለህዝብ ስጋት በማይሆን መልኩ እንዲደመሰስ የድርሻችንን እንወጣለን ብለዋል፡፡

“አንድነታችንን ጠብቀን የኢትዮጵያ ሉዓላዊነትና ነጻነት ለማስጠበቅ እየሰራን ነው" ያሉት አቶ ኢብሳ የአንድ ወር ደሞዛቸውን ለስራዊቱ ድጋፍ ከማድረግ ባለፈ ደም መለገሳቸውንም ገልጸዋል፡፡

ቡድኑ ከተማቸው ድረስ እስኪመጣ መጠበቅ እንደሌለባቸው ጠቁመው "ለአገሬና ለህዝቤ ስል ግንባር ድረስ ሂጄ ቡድኑን ፊት ለፊት ለመፋለም ዝግጁ ነኝ" ብለዋል፡፡

አካባቢያቸውንም ተደራጅተው ከመጠበቅ ባለፈ አጠራጣሪ ነገር ሲመለከቱ ለጸጥታ መዋቅሩ ጥቆማ እየሰጡ መሆናቸውንም ገልጸዋል፡፡

የምእራብ አርሲ ዞን ምክትል አስተዳዳሪ አቶ አቡ ደብረ ማን ገመዳ በበኩላቸው አሸባሪውን ቡድን ለመደምሰስ የዞኑ ህዝብ በየደረጃው የሚያደርገው ሁለተናዊ ድጋፍና ግንባር ለመሄድ ያሳየው ቁርጠኝነት የሚደነቅና ተጠናክሮ መቀጠል ያለበት ነው ነው ያሉት፡፡

አገር ለማፍረስ ሌት ተቀን የሚሰራውን የጥፋት ኃይል በጋራ ለመቅበርና ወደ ልማት ለመዞር ሁሉም የየድርሻውን ሊወጣ እንደሚገባም አሳስበዋል።

ይህን አረመኔ ቡድን ለመጨረሻ ጊዜ ለመቅበር የዞኑ የመንግስት ሰራተኞች ከአንድ ወር ደሞዛቸውን 10 ሚሊዮን ብር ለመከላከያ ስራዊቱ ለመደገፍ ቃል መግባታቸውን ገልጸዋል።

የምዕራብ አርሲ ዞን አስተዳደር ለመከላከያ ስራዊቱ ከ49 ሚሊዮን ብር በላይ ገቢ ለመሰብሰብ አቅዶ እየሰራ ሲሆን እስከ አሁን ከ11 ሚሊዮን ብር በላይ መሰብሰቡን ከዞኑ ያገኘነው መረጃ ያመለክታል፡፡
በውይይቱ ላይ በየደረጃው ያሉ አመራሮች፤ የመንግስት ሰራተኞችና ባለድርሻ አካላት ተገኝተዋል።

የኢትዮጵያ ዜና አገልግሎት
2015
ዓ.ም