“ከባለቤቱ ያወቀ ቡዳ ነው” - ኢዜአ አማርኛ
“ከባለቤቱ ያወቀ ቡዳ ነው”
“ከባለቤቱ ያወቀ ቡዳ ነው”
በመንግስቱ ዘውዴ (ኢዜአ)
የህወሃት የሽብር ቡድን ኢትዮጵያን ለማፍረስ ያለውን የቆየ ውጥን እውን ለማድረግ በምሁርነት፣ በማህበረሰብ አንቂነት፣ በዲፕሎማትነት፣ በጋዜጠኝነት፣ በተንታኝነት፣ በተጽዕኖ ፈጣሪነት፣ በሰብዓዊ ድጋፍ አቅራቢ ድርጅት መሪነት፣ በሰብዓዊ መብቶች ተቆርቋሪነት እና በፖለቲካ ፓርቲ መሪነት ስም የሚጠሩ በርካታ ጀሌዎቹን በመሳሪያነት ሲጠቀም ቆይቷል፡፡
የሽብር ቡድኑ በመሳሪያነት እና በጉዳይ አስፈጻሚነት ከሚጠቀምባቸው እና ከቡድኑ ጋር የቆየ የጥቅም ትስስር ካላቸው ግለሰቦች መካከል አንዱ ማርቲን ፕላውት ነው፡፡ ይህ ግለሰብ ከሽብር ቡድኑ ጋር ያለውን የጥቅም ግንኙነት ለመሸፈን እንዲረዳው ራሱን በእንግሊዝ የሚገኘው የኮመን ዌልዝ ኢንስቲትዩት ባልደረባ እንዲሁም የደቡብ አፍሪካ እና የአፍሪካ ቀንድ ጉዳዮች ተንታኝ እና ተመራማሪ እያለ ይጠራል፡፡ ይህ ግለሰብ የሽብር ቡድኑ የሚሰጠውን ተልዕኮ እየተቀበለ በግል የቲውተር ገጹ መገናኛ ብዙሃንን በመጠቀም ያሰራጫል፡፡ ማርቲን ፕላውት የሽብር ቡድኑ የሚፈጽማቸውን የሽብር ተግባራት ህጋዊ ሽፋን እንዳላቸው ለማስመሰል ጥረት እንደሚያደርግ የሚጽፋቸው ጽሁፎች ይጠቁማሉ፡፡
የቅርቡን ለማንሳት ያህል የአሜሪካ ተራድኦ ድርጅት (USAID) የኢትዮጵያ ሚሽን ዳይሬክተር ሾን ጆንስ ከኢቲቪ ጋር በነበራቸው ቆይታ የሽብር ቡድኑ ከተረጂዎች ላይ እርዳታን በሃይል እየነጠቀ መሆኑን፣ የአሸባሪው ህወሓት ቡድን አባላት ሰርገው በገቡባቸው አካባቢዎች ሁሉ ያሉትን የእርዳታ መጋዘኖች መዝረፋቸውን፣ መኪኖች መስረቃቸውን፣ በየመንደሮቹ ብዙ ውድመት ማድረሳቸውን ይህም በትክክለኛ እና በተጨባጭ መረጃ ላይ የተመሰረተ ስለመሆኑ ገልጸዋል፡፡ ይህ የሽብር እና የዘረፋ እንቅስቃሴ ለተጎጂዎቹም ሆነ ለዕርዳታ አቅራቢው ድርጅት እጅግ አሳሳቢ መሆኑን ሀላፊው ገልጸዋል፡፡
የአሜሪካ ተራድኦ ድርጅት የኢትዮጵያ ሚሽን ዳይሬክተር ሾን ጆንስ በአማራ ክልል የሚገኙ የዕርዳታ ቁሳቁስ ማከማቻ መጋዘኖች በሽብር ቡድኑ መዘረፋቸውን በተጨባጭ መረጃ ላይ ተመስርቶ ትላንት እና ዛሬ የሰጠውን መግለጫ ለማድበስበስ እና ለሽብር ቡድኑ ያላቸውን አጋርነት ለማሳየት በሚመስል መልኩ በአዲስ አበባ የሚገኘው የአሜሪካ ኤምባሲ ባለፉት ዘጠኝ ወራት በነበረው ውጊያ ላይ ተሳታፊ በነበሩ አካላት እንዲሁም ከወራት በፊት የኢትዮጵያ እና የኤርትራ ሰራዊቶች በክልሉ በጥምረት ይሰሩ በነበረበት ወቅት የዕርዳታ ቁሳቁሶች ሲዘረፉ ነበር የሚል ይዘት ያለው መግለጫ ማውጣቱ አስተዛዛቢ እና በሰብዓዊ ድርጅቶች ሚና ውስጥ የፖለቲካ ተቋማቱ ተጽዕኖ ምን ህል እንደሆነ ማሳያም ሆኖ መቅረብ የሚችል መግለጫ ነው፡፡
ይህን የኤምባሲውን መግለጫ ተከትሎም ትላንት ለኢትዮጵያ ቴሌቭዥን መግለጫ የሰጡት የተራድኦ ድርጅቱ ሀላፊ በቲውተር ገጻቸው ላይ ቀደም ሲል የሽብር ቡድኑ ወረራ በፈጸመባቸው የአማራ ክልል በሚገኙ የድርጅቱ መጋዘኖች ላይ አሁንም ዘረፋ እየፈጸሙ መሆናቸውን የሚወጡ አዳዲስ መረጃዎች እየጠቆሙ ነው ብለዋል፡፡
ሀላፊው በሚያውቁት እውነት እና ባላቸው የተረጋገጠ መረጃ ላይ ተመስርተው የተናገሩትን እና በርካታ ዓለም አቀፍ መገናኛ ብዙሃን ሽፋን የሰጡትን የሽብር እና የዘረፋ ተግባር የሽብር ቡድኑ ጀሌ ማርቲን ፕላውት በግል ቲውተር ገጹ ላይ “ይህን ጉዳይ ዘረፋ አልለውም ምክንያቱም እየተካሄደ ያለው ጦርነት ነው በጦርነት ውስጥ ደግሞ ረሃብ አለ” “I am not sure I would have used the term “looted”. This is a war. And people are starving” በማለት ነበር የዕርዳታ አቅራቢው ድርጅት ይፋ ያደረገውን እውነት ለማደባበስ እና የሽብር ቡድኑን ወንጀል ለመከላክል ጥረት አድርጓል። ይህም “ከባለቤቱ ያወቀ ቡዳ ነው” የሚል ብሂል ውስጥ ይከታል።
ማርቲን ፕላውትን እና የሽብር ቡድኑ አፈ-ቀላጤ ጌታቸው ረዳን ከሚያመሳስሏቸው በርካታ ጉዳዮች መካከል አንዱ እና ዋነኛው በፌዴራል መንግስቱ ላይ በተለይም በጠቅላይ ሚኒስትር ዶክተር አቢይ አህመድ ላይ በሚሰነዝሩት ትችት ነው፡፡
በዚህም ጌታቸው ረዳ ከሚሰጣቸው መግለጫዎች ከ50 በመቶ በላይ የሚሆነውን ሰዓት የሚያባክነው ጠቅላይ ሚኒስትር ዶክተር አቢይ አህመድን በመዝለፍ እና በመተቸት ነው፡፡ ማርቲን ፕላውትም እንዲሁ ቀደም ሲል ከሽብር ቡድኑ የሚሰጡትን ተልዕኮዎች ለመወጣት በሚያደርገው ጥረት እና በሚያወጣቸው መረጃዎች ሁሉ የፌዴራል መንግስቱን በተለይ ደግሞ ጠቅላይ ሚኒስትር አቢይን ለመተቸት የሚሰነዝራቸው ትችቶች ይጠቀሳሉ፡፡
ኢትዮጵያ ማንም አካል በውስጥ ጉዳዬ ጣልቃ እንዲገባ አልፈቅድም ግልጽ የሉዓላዊነት ጥሰት ነው እያለች ባለችበት በዚህ ወቅት ይኸው ሰው የአሜሪካ የምስራቅ አፍሪካ ልዩ መልዕክተኛ ጄፍሪ ፌልትማን ወደ ኢትዮጵያ እንደሚመጡ በተሰማበት ወቅት “Interesting, Did you somehow forget that the war began when Tigray was invaded by Ethiopian, Eritrean, Somali and Amhara forces?” በማለት እንዲሁም የሽብር ቡድኑ አሁን ከገባበት አጣብቂኝ መውጣት የሚችለው እና ወደ ቀድሞ የስልጣን መንበሩ መመለስ የሚችለው አሜሪካ በምታደርገው ጣልቃ ገብነት እና በምትፈጥረው ጫና እንደሆነ የተረዳ በሚመስል መልኩ “The U.S. Needs Sharper Tools to Stop the War in Ethiopia” የሚል ሀሳብ በማንሸራሸር የሽብር ቡድኑ ቀኝ እጅ ስለመሆኑ ማረጋገጫ ሰጥቷል፡፡
በተጨማሪም የሽብር ቡድኑ የሌለውን ሀይል እና የውጊያ ብቃት እንዲሁም ያላስመዘገበውን ወታደራዊ ድል ለማንጸባረቅም ጭምር “If this map is correct, then the Tigray Defence Forces are around 20 kilometres from cutting the road that links Amhara. A critical moment?” ከዚህ በተጨማሪም “How does one explain the collapse of the Ethiopian and Eritrean armies in the face of the Tigrayan onslaught in June? Still something of a mystery. But here’s a thought: Napoleon Bonaparte once said, “In war, the moral is to the physical as three is to one.” የሚሉ መረጃዎችን በግል ቲውተር ገጹ እና በሚያገኛቸው የዓለም አቀፍ ብዙሃን መገናኛዎች ጭምር በማንጸባረቅ ለሽብር ቡድኑ ያለውን አጋርነት በግልጽ አሳይቷል፡፡
የሽብር ቡድኑ ወረራውን እና ጥቃቱን በአፋር እና በአማራ ክልሎች ላይ እየፈጸመ መሆኑ እየታወቀም ጭምር ወደ ትግራይ ክልል የዕርዳታ ቁሳቁስ እንዳይገባ ያገደው የኢትዮጵያ መንግስት ነው የሚለውን አሰልቺ የአሜሪካ እና የአንዳንድ ምዕራባውያን ሀገራት መግለጫ “This is one of most direct international statements yet on Ethiopia's intensifying civil war. USAID chief slams federal government for blocking aid to Tigray and calls on the other three main parties to the conflict to withdraw their forces.” የሚል መረጃ በማውጣት ለሽብር ቡድኑ ድጋፉን ለማሳየት ጥረት ሲያደርግ ተስተውሏል፡፡
ይህ የሽብር ቡድኑ አጋፋሪ ከየትኛውም አካል የሚመጣ ማንኛውም የዕርዳታ አቅርቦት ወደ ክልሉ የሚላከው በአዲስ አበባ ቦሌ ዓለም አቀፍ አውሮፕላን ማረፊያ በኩል ተገቢው ፍተሻ ተደርጎለት ብቻ ነው የሚለውን የመንግስት መመሪያ በሚጻረር መልኩ ከተባበሩት አረብ ኤሜሬቶች የመጣ ዕርዳታን በተመለከተ “Very welcome, but why is the UAE allowed to undertake this flight, but (as I understand it) western suggestions of an air-bridge have been ruled out by the Ethiopian government?” የሚል አስተያየት ሰንዝሯል፡፡
ይህ ግለሰብ ከጌታቸው ረዳ ቀጥሎ የሽብር ቡድኑ ሁለተኛ ቃል-አቀባይ ሆኖ እያገለገለ እንደሆነም የሚያመላክቱ የተባባሪነት ተግባራትን እየፈጸመ ይገኛል፡፡ ለዚህም በየጊዜው በሽብር ቡድኑ የሚወጡ መረጃዎችን እና መግለጫዎችን በማስተጋባት ይታወቃል፡፡ ለምሳሌ “Fresh report of a Tigrayan offensive to cut Djibouti-Addis road” እና መሰል መግለጫዎችን በማጋራት እና ያለውንም ድጋፍ በመግለጽ ጭምር ለሽብር ቡድኑ ያለውን አጋርነት በግልጽ አሳይቷል፡፡
ይህ የሽብር ቡድኑ ጡረተኛ የሽብር ቡድኑ እየፈጸመ ያለው ወንጀል እና በፌዴራል መንግስቱ እና በሽብር ቡድኑ መካከል ያለው ችግር በሰላማዊ መንገድም ሆነ በማናቸውም ሁኔታዎች ቢቋጭ ጥቅሙ እንደሚቋረጥ ስለሚያውቅ ግጭቱ እንዲቀጥል ከመፈለጉ የተነሳ“Can the Tigray war will be ended by negotiations?” የሚል አስተያየት ያዘለ ጥያቄ በማንሳት የሽብር ቡድኑ በእኩይ ተግባሩ እንዲቀጥል ሲያበረታታ ተስተውሏል፡፡
ቀደም ሲል የሽብር ቡድኑ ከፌዴራል መንግስቱ ጋር ለድርድር የምቀመጠው ያስቀመጥኳቸው ቅድመ-ሁኔታዎች በሙሉ ከተከበሩ ነው የሚል ሃሳብ መሰንዘሩ ይታወሳል፡፡ ይኸው የሽብር ቡድኑ ጀሌ በአንድም ሆነ በሌላ መንገድ ይህንኑ አቋም ሲያንጸባርቅ ስለመቆየቱ “How about a different headline? STOP ERITREAN AGGRESSION AGAINST TIGRAY! Pull troops out. Open negotiations with Tigray’s government. Allow food and other aid through. Save lives” በማለት በቲውተር ገጹ ላይ ያሰፈረው ጽሁፍ ያሳያል፡፡
የሀገራት የሁለትሽ ግንኙነት መቼ እና እንዴት የሚሉትን አካሄዶች በውል የሚገነዘበው ይህ ግለሰብ ኢትዮጵያ ከጎረቤት ሀገራት እና ከሌሎች አጋር ሀገራት ጋር የምታደርገውን የሁለትሽ ግንኙነት ሁሉ በህወሃት አይን እያየ አሉታዊ አስተያየት ሲሰጥም ተስተውሏል፡፡ ለዚህም በቅርቡ ጠቅላይ ሚኒስትር አቢይ አህመድ ከቱርኩ ፕሬዚደንት ረሲብ ጠይብ ኤርዶጋን ጋር በአንካራ የነበራቸውን ቆይታ በተመለከተ “Critical cooperation or drones?” በማለት እንዲሁም የሶማሊያው ወታደራዊ አዛዥ ከኢትዮጵያ አቻቸው ጀነራል ብርሃኑ ጁላ ጋር ያደረጉትን የሁለትዮሽ ውይይት በተመለከተ “More Somali troops to be sent to Ethiopia? I wonder” የሚል ትችት ያዘለ አስተያየት በመሰንዘር ለማጥላላት ያደረገውን ጥረት በማሳያነት ይነሳል፡፡
ይህ ግለሰብ ከሽብር ቡድኑ ህወሃት ጋር ባለው የጥቅም ግንኙነት ምክንያት የሽብር ቡድኑ የወደደውን የመውደድ እንዲሁም የጠላውን የመጥላት ግዴታ ያለበት መሆኑን የሚያሳይም መረጃ እንዲሁ ሲያሰራጭ ይታያል፡፡ ለማሳያነትም በቅርቡ የሽብር ቡድኑ ከሌላው የሽበር ቡድን ሸኔ ጋር የፈጸመውን ጥምረት በተመለከተ “Ethiopia: Oromo rebels announce an alliance with Tigrayans against PM Abiy. An important development” በማለት እንዲሁም “OLA has continued operating check points along the vital Ethiopia-Kenya road w/ complete impunity. Video below shows fighters guarding a queue for a checkpoint further up the road. The government has yet to respond to what is, frankly, an embarrassing loss of control.” የሚሉ አድናቆት እና ደስታ የተቀላቀለበት አስተያየት አስፍሯል፡፡
ማርቲን ፕላውትን ጨምሮ መሰል የኢትዮጵያ ጠላቶች ስማቸውን በተለያየ ጭንብ በመሸፈን የሽብር ቡድኑ ተከፋይ እና ዓላማ ተጋሪ የሆኑ ግለሰቦች እና ተቋማት በየአቅጣጫው ሲውተረተሩ ይታያል፡፡ እነዚህን መሰል ጠላቶች መመከት የሚቻለው ደግሞ በሀገር ላይ እየደረሰ ያለውን ጫና እና ጣልቃ ገብነት በአግባቡ በመረዳት ሁሉም በተሰማራበት የስራ መስክ ውጤታማ ስራ ሲሰራ እና የሚሰነዘሩ ጫናዎችን የተለያዩ የመረጃ ማሰራጫ አውታሮችን በመጠቀም ተገቢውን ምላሽ መስጠት ሲቻል በመሆኑ ሀገር ወዳድ የሆነ ሁሉ ንቁ ተሳትፎ ማድረግ እንደሚገባው መንግስትን ጨምሮ በርካቶች ይመክራሉ፡፡