አገር ለማፍረስ የተነሳውን አሸባሪ ሃይል በመመከት ለአገራችን ህልውና ተዘጋጅተናል

70

አዲስ አበባ፣ ነሀሴ 25/2013(ኢዜአ) በልደታ ክፍለ ከተማ ከ1 ሺህ በላይ ሴቶች በአገራዊ ወቅታዊ ጉዳዮች ላይ ተወያይተዋል።

በክፍለ ከተማው ከተለያዩ ወረዳዎች የተውጣጡ ሴቶች ኢትዮጵያ በገጠማት ወቅታዊ ፈተና እና መፍትሄዎቹ ላይ በማተኮር መክረዋል።

የክፍለ ከተማው ብልጽግና ፓርቲ ሴቶች ሊግ ሰብሳቢ ወይዘሮ እጅጋየሁ አድማሱ፤ በኢትዮጵያ ህልውና ላይ የተደቀነውን ወቅታዊ ችግር ለመሻገር የሴቶች ተሳትፎና እገዛ ወሳኝ መሆኑን ገልጸዋል።

ከሐሰተኛ መረጃዎች በመራቅ መንግሥት በሚያስፈልገው ድጋፍ ሁሉ ከጎኑ በመቆም አገራዊ ሃላፊነታችንን መወጣት አለብን ብለዋል። 

ከውይይቱ ተሳታፊዎች መካከል ወይዘሮ አሰገደች ሀሩር "ህዝብ መኖር የሚችለው ሀገር ሰላም ሲሆን ነው" ብለዋል።

በመሆኑም አሸባሪውን የህወሃት አጥፊ ኃይል ለማስወገድ ሁላችንም በቻልነው ሁሉ መሰለፍ አለብን ብለዋል።

በውይይቱ ላይ የተሳተፉት ሴቶች በአገር ህልውና ዘመቻው በየትኛውም መልኩ ለመሰለፍ ዝግጁ መሆናቸውንም አረጋግጠዋል።

ሴቶች በተሰማሩበት ሁሉ ውጤታማ በመሆን እንዲሁም ሰራዊቱን በማገዝና በመደገፍ በንቃት እንዲሳተፉ ጥሪ ቀርቧል።

የኢትዮጵያ ዜና አገልግሎት
2015
ዓ.ም