ኢትዮጵያ አሸንፋ ወደ ዕድገት እንድትጓዝ ህይወታችንን ለመስጠት ተዘጋጅተናል -ምልምል የሠራዊት አባላት - ኢዜአ አማርኛ
ኢትዮጵያ አሸንፋ ወደ ዕድገት እንድትጓዝ ህይወታችንን ለመስጠት ተዘጋጅተናል -ምልምል የሠራዊት አባላት
ድሬዳዋ ነሐሴ 23/2013(ኢዜአ) ኢትዮጵያ አሸንፋ ወደ ዕድገት እንድትጓዝ ህይወታቸውን ለመስጠት ዝግጁ መሆናቸውን አስተያየታቸው ለኢዜአ የሰጡ በሰላም ማስከበር ማዕከል የሁርሶ የኮንቲጀንት ማስልጠኛ ትምህርት ቤት ምልምል የሠራዊት አባላት ገለጹ።
ለምልምል የሠራዊቱ አባላት ዛሬ የደቡብ ክልል የኪነ-ጥበብ ዝግጅት አቅርቧል፡፡፡
ምልምል የሠራዊት አባላቱ ለኢዜአ እንደተናገሩት የኢትዮጵያ በአሸናፊነት እንድትወጣ በሚደረገው ሁለንተናዊ እንቅስቃሴ የህይወት መስዋጽትነት ለመክፈል ዝግጁ ተዘጋጅተዋል።
ምልምል ወታደር አጸደ ታዘበ አገር አፍራሽና ባንዳውን ህውሃት ለመደምሰስ ህይወቷን ያለ ስስት ለመስጠት መሰናዳቷን ትናገራለች፡፡
''ሴት ወታደር ሆኜ አገሬን ለማዳን በመታጠቄ ደስተኛ ነኝ ፤ ለሀገሬ ህይወቴን ለመስጠት ዝግጁ ነኝ'' ብላለች፡፡
''አገሬን አድኜ ልማቷ እንዲቀጥል አስፈላጊውን መስዋዕትነት ለመክፈል ዝግጁ ነኝ'' ያለው ደግሞ ምልምል ወታደር አቡሌ ንጉሴ ነው፡፡
ምልምል ወታደር የሺወርቅ አዲስ ''አገሬን ከጦርነት ተገላግላ ሰላሟ እንዲሰፍን በሴትነቴ አስፈላጊውን ሁሉ ለመስጠት ተዘጋጅቼ ነው የመጣሁት'' ስትል አስተያየቷን ሰጥታለች፡፡
ምልምል ወታደሮቹ አሠልጣኞቻቸው ሣይሰለቹ ሌት ተቀን አገርን ለማዳን የሚያስችል ዕውቀት እያስታጠቋቸው መሆኑንም ተናግረዋል፡፡
የደቡብ ኪነ-ጥበብ ቡድን ለቀረበላቸው አዥናኝ ዝግጅትም አመስግነዋል፡፡
የትምህርት ቤቱ አሰልጣኞች እንደሚናገሩት ኢትዮጵያ የገጠማትን ነቀርሳ ከሠራዊቱ ጎን በመቆም ከነርዝራዡ ነቅለው የሚያወጡ ትንታግ ወጣቶች በየማሰልጠኛዎቹ ጥሩ ዕውቀትና ከስብዕና ጋር እየቀሰሙ ናቸው፤ ለእናት አገራቸው መስዋዕት ለመክፈል ተዘጋጅተዋል ይላሉ፡፡
አሰልጣኝ መቶ አለቃ መሐመድ ኢልያስ ''ትንታግ ወጣቶች እያፈራች ያለች አገርና ሌት ተቀን የሚሞትላት ጀግና ሠራዊት ያላት አገር የገጠማትን ወቅታዊ ችግር በድል ትሻገራለች'' በወጣቶቹ ያላቸውን እምነት ይናገራሉ ፡፡
የሁርሶ ወታደራዊ ማሰልጠኛ ትምህርት ቤት በአገርና በአለም አቀፍ ደረጃ ታላላቅ ጀብድና የአገርን ሉዓላዊነትን ያስከበሩ ጀግኖች መፍለቂያ መሆኑ ይታወቃል፡፡