የህወሓት አሸባሪ ቡድን እስከሚጠፋ ለኢትዮጵያ ህልውና ስንል ድጋፋችን ይቀጥላል - ኢዜአ አማርኛ
የህወሓት አሸባሪ ቡድን እስከሚጠፋ ለኢትዮጵያ ህልውና ስንል ድጋፋችን ይቀጥላል
አዲስ አበባ፤ ነሀሴ 23 ቀን 2013 (ኢዜአ) የህወሓት አሸባሪ ቡድን እስከሚጠፋ ለኢትዮጵያ ህልውና ስንል ድጋፋችን ይቀጥላል ሲል የኢትዮጵያ መስማት የተሳናቸው ብሔራዊ ማህበር ገለጸ።
የማኅበሩ አመራሮችና ሰራተኞችና እንዲሁም አባላቱ ለአገር መከላከያ ሰራዊት የአንድ ወር ደሞዛቸውን፣ የስንቅ ድጋፍና የደም ልገሳ አድርገዋል።
የማህበሩ ፕሬዝዳንት ዶክተር ጳውሎስ ካሱ፤ በዚሁ ወቅት ባስተላለፉት መልእክት የህወሓት አሸባሪ ቡድን እስከሚጠፋ ለኢትዮጵያ ህልውና ስንል ድጋፋችን ይቀጥላል ብለዋል።
ማህበሩ በቀጣይም ለመከላከያ ሠራዊት የሚችለውን ሁሉ ድጋፍ ለማድረግ ዝግጁ መሆኑን አረጋግጠዋል።
የመከላከያ ሰራዊት ድጋፍ አሰባሳቢ ኮሚቴ ሰብሳቢ ብርጋዴር ጀኔራል አስረስ አያሌው፤ የኢትዮጵያ መስማት የተሳናቸው ብሔራዊ ማህበር አመራሮችና ሰራተኞች ላደረጉት ድጋፍ አመስግነዋል።
አሸባሪው ህወሓት ከውስጥና ከውጭ ሃይሎች ጋር በማበር ኢትዮጵያን ለማፍረስ የሚያደርገው እንቅስቃሴ ፈፅሞ እንደማይሳካና በኢትዮጵያዊያን የጋራ ክንድ እነደሚደመሰስ ገልጸዋል።
ለመጪው ትውልድ የተሻለች ኢትዮጵያ እንጂ የተበታተነች አገር ልናስረክብ አይገባም ለዚህም የተዘጋጀ ትውልድ መኖሩን ጠቅሰዋል።
የኢትዮጵያ መስማት የተሳናቸው ብሔራዊ ማህበር ከተመሰረተ ከ50 ዓመታት በላይ ማስቆጠሩን መረጃዎች ይጠቁማሉ።