ቀጥታ፡

የህዝቡ ያልተቋረጠ ድጋፍ ሰራዊቱ የአገሩን ህልውና እንዲያስጠብቅ ትልቅ አቅም ሆኖታል

አዲስ አበባ ነሃሴ 21/2013(ኢዜአ) የኢትዮጵያ ህዝብ እያደረገ ያለው ያልተቋረጠ ድጋፍና ማበረታቻ ሰራዊቱ የአገሩን ህልውና እንዲያስጠብቅ ትልቅ አቅም ሆኖታል ሲሉ የአገር መከላከያ ሰራዊት አባላት ተናገሩ።

አሸባሪው የህወሃት ቡድን ኢትዮጵያን ለማፍረስ እስከ ሲኦልም ቢሆን እገባለሁ ብሎ ጦርነት በማወጁ የአገር መከላከያ ሰራዊት የአገሩን ክብርና ዳር ድንበር ለማስከበር ቆሟል።

የኢትዮጵያ ህዝብም "በአገሬ የመጣ ጠላት ላልምረው" በማለት የትም መቼም በየትም በመዝመት አለኝታነቱን እያሳየ ይገኛል።

በግንባር ተገኝቶ ኢዜአ ያነጋገራቸው የአገር መከላከያ ሰራዊት አባላት የህዝቡ ያልተቋረጠ ድጋፍና እገዛ ለአገራችን ህልውና ለመፋለም ትልቅ የሞራል ስንቅ ሆኖናል፣ ኢትዮጵያን እናስከብራታለን ብለዋል።

አሸባሪውን የህወሃት ቡድን እስከ ወዲያኛው ለማጥፋት ተዘጋጅተናል በማለት ህዝቡ እስከ መጨረሻው ከጎናችን ይቁም ሲሉ ጠይቀዋል።

ዘመቻው የኢትዮጵያን ህዝብ ሰላም የሚነሳውን ኃይል ለማጥፋት የሚደረግ በመሆኑ በህዝባችን እገዛ በድል እንወጣዋለን ሲሉም ነው ያረጋገጡት።

የህወሃት አሸባሪ ሃይል ፕሮፓጋንዳ በመንዛት ከፍ ያለ አቅም ያለው ቢያስመስልም አሁን ላይ ፍጹም የተዳከመ መሆኑንም ጠቁመዋል፡፡

ኢትዮጵያ ስትነካ ህዝቡ በመተባበር የሚሰጠውን ድጋፍ ከዚህ ቀደም በታሪክ የምንሰማው ቢሆንም አሁን ግን በተግባር ተመልክተነዋል ብለዋል የሰራዊቱ አባላት።

የመከላከያ ሰራዊቱ ዋነኛ ኃይል ህዝቡ መሆኑን በማንሳት ህዝቡ ከጎናችን እስካለ ድረስ ወራሪውንና አሸባሪውን ቡድን በአጭር ጊዜ ውስጥ ድባቅ እንመታዋለን ብለዋል፡፡

አሸባሪው ተደምስሶ የኢትዮጵያ አሸናፊነት በቅርቡ ይረጋገጣል ሲሉም ተናግረዋል፡፡

የኢትዮጵያ ዜና አገልግሎት
2015
ዓ.ም