ቀጥታ፡

ለባለ ልዩ ጣዕም ቡና ቅምሻ ውድድር አሸናፊዎች እውቅና ተሰጠ

አዲስ አበባ፤ ነሀሴ 20 ቀን 2013 (ኢዜአ) የኢትዮጵያ ቡናና ሻይ ባለሥልጣን በሁለተኛው ዙር ዓለም አቀፋ የባለ ልዩ ጣዕም ቡና ቅምሻ ውድድር አሸናፊ ለሆኑ አርሶ አደሮችና አስተዋጽዖ ላደረጉ አካላት እውቅና ሰጠ።

አሸናፊ የሆኑት አርሶ አደሮች 1 ነጥብ 9 ሚሊየን ዶላር ለአገሪቱ ገቢ አስገኝተዋል ተብሏል።

ለውድድሩም አርባ አይነት ባለ ልዩ ጣዕም የቡና ዝርያዎች ለውድድር ቀርበው እንደነበር ተገልጿል።

ውድድሩ ለኢትዮጵያን ቡና በዓለም አቀፉ ማኅበረሰብ ለማስተዋወቅ፣ የገበያ እድሎችን ለመፍጠርና አዳዲስ ዝርያዎችን ለማግኘት እድል ፈጥሯል ተብሏል።

በእውቅና መርኃ ግብሩም በልዩ ጣዕም አሸናፊ የሆኑ የቡና ዝርያዎች ቅምሻ ተካሂዷል።

በ2013 ዓ.ም በጀት ዓመት ከቡና፣ ሻይና ቅመማ ቅመም ወጪ ንግድ 927 ዶላር ገቢ መገኘቱ ይታወቃል።

ለዚህም ገቢ መገኘት ከፍተኛ አስተዋጽዖ ለነባራቸው ላኪ ድርጅቶችና ተቋማት እውቅና እና የማበረታቻ ሽልማት በዚሁ ሳምንት ተሰጥቷል።

በ2014 ዓ.ም በጀት ዓመት ከቡና፣ ሻይና ቅመማ ቅመም ወጪ ንግድ ከ1 ነጥብ 2 ቢሊዮን ዶላር በላይ ገቢ ለማግኘት ታቅዷል።

በእውቅና ሥነ-ሥርዓቱ የግብርና ሚኒስትሩ ዑመር ሁሴንን ጨምሮ ሌሎች ከፍተኛ የመንግሥት የሥራ ኃላፊዎች ተገኝተዋል።

የኢትዮጵያ ዜና አገልግሎት
2015
ዓ.ም