ኮሌጁ የልዩ ኃይል ምልምል ፖሊሶችን አስመረቀ - ኢዜአ አማርኛ
ኮሌጁ የልዩ ኃይል ምልምል ፖሊሶችን አስመረቀ
እንጅባራ ነሀሴ 20/2013 (ኢዜአ) የአማራ ክልል ፖሊስ ኮሌጅ ለ8ኛ ዙር በጥሩ ብርሃን መለስተኛ ውትድርና ማሠልጠኛ ማዕከል ያሰለጠናቸውን የልዩ ኃይል ምልምል ፖሊሶች አስመረቀ።
ተመራቂ የልዩ ኃይል ፖሊሶች ከሁሉም የክልሉ ዞኖችና ወረዳዎች ተመልምለው በጦር መሣሪያ አጠቃቀምና በከፍተኛ ወታደራዊ ሥልት የተሰጣቸውን ስልጠና በብቃት ያጠናቀቁ መሆናቸውን በማዕከሉ የ8ኛ ዙር ሠልጣኞች ምክትል አስተባባሪ ኮማንደር መላኩ እሸቴ ለኢዜአ ተናግረዋል።
በተጨማሪም ጠላትን መመከት የሚያስችላቸውን የአካልና የሥነ ልቦና ዝግጅት ያደረጉ መሆናቸውን አመልክተዋል
ተመራቂዎች በሥነ ሥርዓቱ ላይ ወታደራዊ ትርኢቶች አሳይተዋል።
በምረቃ ሥነ ሥርዓቱ ላይ የክልሉ ርዕሰ-መስተዳድር አቶ አገኘው ተሻገር፣ የሰላምና ደህንነት ቢሮ ሃላፊ ዶክተር ሰማ ጥሩነህ፣ የጠቅላይ ሚኒስትሩ የደህንነት ጉዳዮች አማካሪ ሚኒስትር አቶ ገዱ አንዳርጋቸው፣ የገቢዎች ሚኒስትር አቶ ላቀ አያሌውን ጨምሮ ሌሎችም የክልልና ፌደራል የስራ ሃላፊዎች ተገኝተዋል።