ቀጥታ፡

የአሸባሪውን ቡድን እድሜ ለማሳጠር የድርሻችንን እየተወጣን ነው--አርቲስቶች

ደሴ ነሃሴ 19/2013 ( ኢዜአ ) ሙያቸውን በመጠቀም የአሸባሪውን የህሓት ቡድን እድሜ ለማሳጠር የድርሻቸውን እየተወጡ መሆናቸውን በወሎ ግንባር የተሰለፉ አርቲስቶች ገለፁ፡፡
በወሎ ግንባር የተሰለፉ አርቲስቶች አስተባባሪ ድምጻዊ ዩርዳኖስ አለሜ ለኢዜአ እንደገለፀው በአባቶታችን ደምና አጥነት ሉዓላዊነቷና ነጻነቷ የተጠበቀች ሀገር በባንዳ ስትወር መመልከት ህመምና ውርደት ነው።

"የእናት ጡት ነካሹ የህወሓት ቡድን በህዝብና በሀገር ላይ ጉዳት ቢያደርስም እኛ የኢትዮጵያ ልጆች በህይወት እያለን አይሳካለትም" ብሏል፡፡

"ቡድኑ ሰርጎ በገባባቸው የአማራና የአፋር ክልሎች ህዝቡን በግፍ ከመጨፍጨፉ ባለፈ ዘረፋና ውድመት እያደረሰ በመሆኑ ትግስታችን ተሟጧል" ሲል ተናግሯል።

የቡድኑን እድሜ ለማሳጠርና የህብረተሰቡን መከራና ሰቆቃ ለመታደግ ግንባር የሚፋለመውን ሰራዊት በኪነ ጥበብ ለማነቃቃት ወሎ ግንባር መገኘታቸውን ገልጻል።

"የአርቲስት ልዑኩ ከመከላከያና ባለድርሻ አካላት ጋር ተቀናጅቶ ወደ ስራ ገብቷል" ያለው አስተባባሪው "ኢትዮጵያን ከመፈራረስ ለመታደግ ከስራዊቱ ጎን ተሰልፈን እስከ ህይወት መስዋእት ለመክፈል ተዘጋጅተናል" ሲል  አስታውቋል፡፡

ሌላው አርቲስት ኑር አዲስ ሰይድ በበኩሉ "አሸባሪው ቡድን የፀነሰውን ሴራና የሚፈጽመውን ግፍ ከበፊት ጀምሬ ለህብረተሰቡ በጥበብ ሳሳውቅና ሳነቃ ቆይቻለሁ፤ እንግልትና መከራም ደርሶብኛል" ብሏል፡፡

የህወሓት ቡድን የእሳካሁኑ በደልና ግፍ አልበቃው ብሎ አሁንም በአማራና በአፋር ህዝብ ላይ አሰቃቂ ድርጊት ከመፈጸሙም ባለፈ ቤት ማቃጠል፣ ዘረፋና ስርቆት እየፈመ መሆኑን ተናግሯል፡፡

"የቡድኑን አስነዋሪ ተግባር ለመጨረሻ ጊዜ ለማስቆም ሙያዊ ግዴታችንን ከመወጣት ባለፈ እስከ ህይወት መስዋእት በመክፈል የኢትዮጵያን ሉዓላዊነትና ነጻነት ለማስጠበቅ የድርሻችንን እንወጣለን" ብሏል።

በተለያዩ የኪነ ጥበብ ስራዎች ስራዊቱን በማበረታታትና በማነሳሳት እንዲሁም ደጀን በመሆንና ስንቅ በማቀበል ጭምር በግንባር ተገኝተው ቡድኑን በመፋለም ተግባር የድርሻቸውን እየተወጡ መሆናቸውን ተኗግሯል።

"የህወሓት አሸባሪ ቡድን በብሔር ብሄረሰቦች ላይ ያልፈጸመው ግፍ የለም፤ አንድነታችን ጠብቀን ቡድኑን መቅበርና ነጻነታችንን ማወጅ ይኖርብናል" ያለው ደግሞ አርቲስት አየለ ጌታቸው ነው፡፡

"ያለ ሀገር መስራትም ሆነ መኖር ስለማይቻል ቡድኑን ዳግም ስጋት በማይሆን መልኩ በጋራ ተረባርበን መደምሰስ ይኖርብናል" ሲል ገልጿል።

ቡድኑ ለመጨረሻ ጊዜ እንዲቀበር ሁሉም የሚችለውን ማድረግና ከስራዊቱ ጎን መቆም እንደሚገባው አስገንዝቧል።

እኔም በኦሮሞኛና በተለያዩ ቋንቀቋዎች ስራዊቱን በማበረታታት፣ ሞራል በመስጠት፣ ደጀንነቴን በተግባር በማሳየትና በመደገፍ ሀገራዊ ግዴታዬን ለመወጣት ግንባር ተገኝቻለሁ" ሲል አስታውቋል።

የኢትዮጵያ ዜና አገልግሎት
2015
ዓ.ም