ባለስልጣኑ 2014 በጀት ዓመት 1 ነጥብ 2 ቢሊዮን ዶላር ገቢ ለማግኘት እቅድ መያዙን አስታውቋል - ኢዜአ አማርኛ
ባለስልጣኑ 2014 በጀት ዓመት 1 ነጥብ 2 ቢሊዮን ዶላር ገቢ ለማግኘት እቅድ መያዙን አስታውቋል
ነሃሴ 18/2013 (ኢዜአ) የኢትዮጵያ ቡናና ሻይ ባለስልጣን በ2014 በጀት ዓመት 1 ነጥብ 2 ቢሊዮን ዶላር ገቢ ለማግኘት ማቀዱን አስታወቀ።
በተጠናቀቀው በጀት ዓመት በቡና፣ ሻይና ቅመማ ቅመም ምርቶች ከፍተኛ የኤክስፖርት አፈፃጸም ላስመዘገቡ ላኪ ድርጅቶችና ተቋማት እውቅና እየሰጠ ነው።
በእውቅና ስነ-ስርዓቱ ላይ የግብርና ሚኒስትሩ አቶ ዑመር ሁሴን፣ የግብርና ሚኒስትር ዴዔታዋ አይናለም ንጉሴ፣የጉምሩክ ኮሚሽነር ደበሌ ቃበታ እና ሌሎች ጥሪ የተደረገላቸው እንግዶች ተገኝተዋል።
እውቅናው ከተሰጣቸው መካከል የቡና፣ ሻይና ቅመማ ቅመም ምርቶችን የሚልኩ ድርጅቶች፣ አቅራቢዎች፣ የህብረት ስራ ዩኒየኖች እንዲሁም አርሶ አደሮች ይገኙበታል።
የኢትዮጵያን ቡና በዓለም አቀፉ ማህበረሰብ ለማስተዋወቅ፣ የገበያ እድሎችን ለመፍጠር እና አዳዲስ ዝርያዎችን ለማግኘት ሁለተኛ ዙር የባለ ልዩ ጣዕም ቡና ቅምሻ ውድድር መካሄዱ ይታወሳል።
ጥራታቸው ልዩ የሆኑ 30 የቡና ዝርያዎች በውድድሩ ተመርጠው በዓለም አቀፍ ግልጽ ጨረታ ሽያጭ 1ነጥብ 8 ሚሊዮን የአሜሪካን ዶላር ገቢ ማስገኘታቸውን ከባለስልጣኑ ያገኘነው መረጃ ያመለክታል።
ባለስልጣኑ በተጠናቀቀው የ2013 በጀት ዓመት ከቡና ወጪ ንግድ 907 የአሜሪካን ዶላር የውጭ ምንዛሬ ገቢ ማግኘቱም የሚታወስ ነው።