ቀጥታ፡

በሶማሌ ክልል ለፖለቲካ ጥቅም ሲባል ተቀነባብሮ የተፈጠረው ችግር ህዝብን እንደማይወክል የክልሉ ተወላጆች ገለጹ

አዲስ አበባ ነሀሴ 5/2010 በሶማሌ ክልል የተፈጠረው ችግር ለፖለቲካ ጥቅም የተቀነባበረ እንጂ የክልሉን ህዝብ የሚወክል እንዳልሆነ የክልሉ ተወላጆች አስታወቁ። ችግሩ ባስከተለው ጉዳት ማዘናቸውን የገለፁት ተወላጆቹ የፌዴራል መንግስት የወሰደው እርምጃ ትክክል መሆኑንና የችግሩ ጠንሳሽ የሆኑ አካላትን ለህግ ማቅረብ እንደሚገባ ተናግረዋል። የክልሉ ተወላጆች የሆኑት የህክምና ተማሪ መሃመድ ሃሰን አብዲ እና የህዝብ ተወካዮች ምክር ቤት ተመራጭ የነበሩት አሊ አፊ አሊ   ከአሁን በፊትም በርካታ የሰብአዊና ዴሞክራሲያዊ መብት ጥሰቶች እየተፈፀመባቸው እንደነበር አስታውሰው እየደረሰ ያለውን ጥሰት የአገር ሽማግሌዎችና የሃይማኖት አባቶች ጭምር ለፌዴራል መንግስት አቅርበው ምላሽ እንዲሰጣቸው መጠየቃቸውን ተናግረዋል። አሁን በክልሉ የተከሰተው ችግር ህዝቡ አጋረዊ ለውጡ እንዲመለከተው ጥያቄ በማንሳቱና የተከማቹ የመልካም አስተዳደርና የዴሞክራሲ ጥያቄው በክልሉ መንግስት ምላሽ እንዲያገኙ ጠንካራ ፍላጎት በማሳየቱ እንደሆነ ገልጸዋል። እንዲሁም የህክምና ተማሪ የሆነው መሃመድ ሃሰን አብዲና አህመድ ሙሃመድ ኢብራሂም  የተባሉት ነዋሪዎች ፌዴራል መንግስቱ የወሰደው እርምጃ ትክክለኛና መሆኑንና እርምጃው  የሶማሌ ህዝብ ሲመኘው የነበረ ነው ብለዋል፡፡ በቀጣይ ክልሉ እንደማንኛውም የኢትዮጵያ ህዝብ እኩል የመሰረተ ልማት የሚያገኝበት፣ የዴሞክራሲያዊና ሰብአዊ መብቱ የሚከበርበት መንግስት መዋቀር እንዳለበትና የፌዴራል መንግስት ከታች እስከላይ ያለውን የክልሉን መንግስት መዋቅር ሊፈትሽና ሊያጠራ እንደሚገ ጠቁመዋል። ከአሁን በፊት የክልሉ ህዝብ የሚያከብራቸውና የሚቀበላቸው የአገር ሽማግሌዎችና የሃይማኖት አባቶችም ከመንግስት ጋር በቅርበት እንዲሰሩና ሁሉም ኢትዮጵያዊ ተሳስቦ የሚኖርበት ክልል መፈጠር አለበት ሲሉም አስተያየታቸውን ሰጥተዋል። የፌዴራል መንግስት በክልሉ የተፈጠረውን ችግር ለማረጋጋት የወሰደው እርምጃ ትክክልና መሆን እንዳለበት ተወላጆቹ እርምጃው ቀደም ብሎ ተወስዶ ቢሆን ችግሩ ላይፈጠር ይችል እንደነበር ገልፀዋል። በቀጣይ ክልሉ እንደማንኛውም የኢትዮጵያ ህዝብ እኩል የመሰረተ ልማት የሚያገኝበት፣ የዴሞክራሲያዊና ሰብአዊ መብቱ የሚከበርበት መንግስት መዋቀር እንዳለበትና የፌዴራል መንግስት ከታች እስከላይ ያለውን የክልሉን መንግስት መዋቅር ሊፈትሽና ሊያጠራ እንደሚገ ጠቁመዋል። ከአሁን በፊት የክልሉ ህዝብ የሚያከብራቸውና የሚቀበላቸው የአገር ሽማግሌዎችና የሃይማኖት አባቶችም ከመንግስት ጋር በቅርበት እንዲሰሩና ሁሉም ኢትዮጵያዊ ተሳስቦ የሚኖርበት ክልል መፈጠር አለበት ሲሉም አስተያየታቸውን ሰጥተዋል። በሶማሌ ክልል የተፈጠረውን ችግር ለመፍታት በአሁኑ ወቅት ኮማንድ ፖስት ተቋቁሞ እየተሰራ ይገኛል።
የኢትዮጵያ ዜና አገልግሎት
2015
ዓ.ም