ቀጥታ፡

በመዲናዋ የተገነባው 6ኛው የምገባ ማዕከል ተመርቆ አገልግሎት መስጠት ጀመረ

ነሐሴ 18 / 2013 (ኢዜአ) በአዲስ አበባ በንፋስልክ ላፍቶ ክፍለ ከተማ የተገነባው ተስፋ ብርሃን የምገባ ማዕከል ተመርቆ አገልግሎት መስጠት ጀመረ።

ማዕከሉ በአዲስ አበባ ደረጃ ስድሰተኛ ሲሆን በዝቅተኛ የኑሮ ደረጃ ላይ የሚገኙ ነዋሪዎችን መመገብ የሚያስችል ነው።

የአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር ምክትል ከንቲባ አዳነች አቤቤ ማእከሉን መርቀው በከፈቱበት ወቅት እንዳሉት የምገባ ማዕከሉ በአንድ ቀን አንድ ሺህ ሰዎችን የመመገብ አቅም አለው።

የማእከሉ መገንባት በችግር ውስጥ ያሉ ዜጎችን ለመደገፍ የተቀመጠው እቅድ አካል መሆኑንም አንስተዋል።

የማዕከሉን የአንድ ዓመት የምገባ ወጪውን ለመሸፈን ከተማዋ ባለሃብት አቶ ሙኒር አይረዲን ቃል ገብቷል፡፡
በመርሐ ግብሩ ላይ ምክትል ከንቲባ ወይዘሮ አዳነች አቤቤን ጨምሮ የመዲናዋ  ከፍተኛ አመራሮች ተገኝተዋል፡፡ 

የኢትዮጵያ ዜና አገልግሎት
2015
ዓ.ም