አሸባሪውን ለመደምሰስ በሚካሄደው ትግል ሁሌም ከሀገር መከላከያ ሰራዊት ጎን ነን! - ኢዜአ አማርኛ
አሸባሪውን ለመደምሰስ በሚካሄደው ትግል ሁሌም ከሀገር መከላከያ ሰራዊት ጎን ነን!
ነሐሴ 15/2013 (ኢዜአ) አሸባሪው ህወሓት በሀገራችን ላይ እያደረሰ ያለውን ጥቃት ለመመከትና ቡድኑን ለመደምሰስ ሁሌም ከመከላከያ ሰራዊት ጎን ነን ሲሉ የምዕራብ አርሲ ዞን ነዋሪዎች አስታወቁ።
ነዋሪዎቹ ሰራዊቱን የሚደግፍ ፣ህወሓትና ሸኔን የሚያወግዝ ሰላማዊ ሰልፍ ዛሬ በአርሲ ነገሌ ከተማ አካሄደዋል።
አሸባሪዎቹ ህወሓት እና ሸኔ የኢትዮጵያ ጠላት ናቸው፣ እኛ ዛሬም ፣ ነገም ወደፊትም ከሀገር መከላከያ ጎን ነን በማለት ድምጻቸውን በጋራ አሰምተዋል።
የምዕራብ አርሲ ዞን ምክትል አስተዳዳሪ አቶ አብድረማን ገመዳ በወቅቱ እንዳሉት ህዝቡ አሸባሪዎቹን ህወሓት እና ሸኔን ለመጨረሻ ጊዜ ለማጥፋት የሚካሄደውን ትግል በመደገፍ የድርሻቸውን እየተወጡ መሆኑን ገልጸዋል።
የመንግሥት ጥሪ ተቀብለው ወደ ግንባር ለመዝመት በዝግጅት ላይ የሚገኙ የዞኑ ወጣቶች ክብር እና ምስጋና እንደሚገባቸውም ተናግረዋል።
ኢትዮጵያን እረፍት እየነሱ የሚገኙት አሸባሪ ቡድኖቹን በማስወገድ ህዝቡ ፊቱን ወደ ልማት መመለስ አለበት ብለዋል።
በተለይ የሀገራችን መገለጫ የሆነው የህዳሴ ግድቡን እስከ ፍፃሜ ሰርተን ያለንን አንድነት በድጋሜ ለአለም ማሳየት ይኖርብናል ነው ያሉት።
በሰልፉ ላይ ከዞኑ ሁሉም ወረዳዎች እና ከተማ አስተዳደሮች የተወጣጡ ነዋሪዎች ተሳትፈዋል።