ቀጥታ፡

የወልቃይት ጠገዴ ሕዝብ አሸባሪውን ህወሕት ለአንዴና ለመጨረሻ ጊዜ ለመደምሰስ እየታገለ ነው

አዲስ አበባ ነሃሴ 15/2013(ኢዜአ) የወልቃይትና ጠገዴ ሕዝብ አሸባሪውን የህወሓት ቡድን "ለአንዴ እና ለመጨረሻ ጊዜ ለመደምሰስ አፅንኦት ሰጥቶ እየታገለ ነው" ሲሉ የወልቃይት ጠገዴ ሰቲት ሁመራ ዞን ዋና አስተዳዳሪ አቶ አሸቴ ደምለው ተናገሩ።

ዋና አስተዳዳሪው አሸባሪው ህወሓት በዞኑ ነዋሪዎች ላይ ያደረሰው ግፍና በደል 'ታሪክ የማይረሳው ነው' ሲሉ ለመገናኛ በዙሃን ገልጸዋል።

በሕዝብ ላይ ያደረሰው ግፍ እና በደል አልበቃ ብሎት በአገር መከላከያ ሠራዊት የሰሜን ዕዝ ላይ የፈፀመውን ጥቃትም አስታውሰዋል።

"አሸባሪው ህወሓት የክፋት ጥግ ማሳያ የወልቃይት ጠገዴ ሕዝብ ነው" ያሉት አቶ እሸቴ፤ አሸባሪው ቡድን በአካባቢው በሕይወት ያለን የሰው ልጅ የቀበረ ነው ብለዋል።

ቡድኑ በማይካድራ የፈጸመው የዘር ማጥፋት ድርጊት ስድስት የሚሆኑ የጅምላ መቃብሮች በተሪካን አየር ማረፊያ እንደሚገኙ ገልፀዋል።

የወልቃይት ጠገዴ ሕዝብ የአሸባሪውን ህወሓት ሴራ ጠንቅቆ የሚያውቅ በመሆኑ ከኢትዮጵያ ምድር ለአንዴ እና ለመጨረሻ ጊዜ እንዲጠፋ ተደራጅቶ እየታገለ እንደሚገኝ ነው የተናገሩት።

አሰቃቂና አረመኔያዊ ድርጊት የተፈፀመበት የአካባቢው ማኅበረሰብ ይህ አሸባሪ ቡድን ዳግም "በኢትዮጵያ ምድር እንዲኖር አይፈቅድለትም" ብለዋል።

አሸባሪው ቡድን በተላላኪዎቹ ትንኮሳ እንዳይፈፅም ሕዝቡ ተደራጅቶ አካባቢውን በንቃት እየጠበቀ እንደሚገኝ ገልጸዋል።

ሕዝቡ ከአገር መከላከያ ሠራዊትና ከጸጥታ ሃይሎች ጋር በመሆን ደጀንነቱን እያሳየ መሆኑንም እንዲሁ።

የአካባቢው ማኅበረሰብ ከህልውና ዘመቻው ጎን ለጎን እርስ በእርስ በመደጋገፍ የዕለት ተዕለት እንቅስቃሴና የእርሻ ስራውን እያከናወነ ይገኛል ነው ያሉት ዋና አስተዳዳሪው።

የመንግስት መስሪያ ቤቶችና አገልግሎት ሰጪ ተቋማት ማኅበረሰቡን እያገለገሉ መሆኑንም ገልጸዋል።

የኢትዮጵያ ዜና አገልግሎት
2015
ዓ.ም