ቀጥታ፡

ተጋሩ ኢትዮጵያን የሚያፀኑ እንጂ የሚያፈርሱ ቡድኖች አካል ሆነው አያውቁም

ነሐሴ 14 / 2013 (ኢዜአ) "ተጋሩ ኢትዮጵያን የሚያፀኑ እንጂ የሚያፈርሱ ቡድኖች አካል ሆነው አያውቁም" ሲሉ የትግራይ ክልል ጊዜያዊ አስተዳደር ዋና ስራ አስፈፃሚ ዶክተር አብርሃም በላይ ተናገሩ።

በአዲስ አበባ የሚኖሩ የትግራይ ተወላጆች ለአገር መከላከያ ሠራዊት ደም በመለገስ አጋርነታቸውን ገልፀዋል።

"ደም ልገሳው የትግራይ ተወላጆች 'በኢትዮጵያዊነታችን የማንደራደር መሆናችንን እንዲሁም ኢትዮጵያን አፅንተን ለማስቀጠል ያለንን ቁርጠኝነት የምናሳይበት ነው" ሲሉ ዶክተር አብርሃም ተናግረዋል።

"አሸባሪው ህወሓት የትግራይን ሕዝብ አይወክልም" ያሉት ዶክተር አብርሃም፤ ቡድኑ የሚያራምደው አጀንዳ ሕዝብን ሊወክል የማይችል የራሱ የጥፋት ሐሳብ እንደሆነ አስገንዝበዋል።

"የትግራይ ሕዝብ ኢትዮጵያን የሚያስቀጥል እንጂ የሽብር እንቅስቃሴ ደጋፊም አይደለም" ብለዋል።

የሽብር ቡድኑ እኩይ ተግባር እንዳይሳካ የኢትዮጵያ ሕዝብ በሚንቀሳቀስበት ጊዜ ተጋሩ ግንባር ቀደም ሆኖ መንቀሳቀስ እንዳለበትም አስገንዝበዋል።

የኢትዮጵያ ዜና አገልግሎት
2015
ዓ.ም