ቀጥታ፡

ቀይ መስቀል አሸባሪው ቡድን በፈጸመው ወረራ ለተፈናቀሉ ወገኖች ድጋፍ አደረገ

ነሐሴ 12/2013 (ኢዜአ) የኢትዮጵያ ቀይ መስቀል ማህበር ጎንደር ቅርንጫፍ የህወሃት አሸባሪ ቡድን በፈጸመው ወረራ ተፈናቅለው በደባርቅ ጊዚያዊ መጠለያዎች ለሚገኙ ወገኖች የቁሳቁስ ድጋፍ አደረገ።

የቅርንጫፉ አስተባባሪ አቶ አታለል ታረቀኝ ለኢዜአ እንደተናገሩት፤  ድጋፉ የተደረገላቸው በወረራው ሳቢያ ከማይጠብሪና አዲ አርቃይ አካባቢዎች ከቤት ንብረታቸው ተፈናቅለው ለመጡ አንድ ሺህ ለሚደርሱ አባወራና ቤተሰቦቻቸው ነው፡፡

ለእነዚህ  ወገኖች 8 ቦንዳ የአዋቂዎችና የህጻናት አልባሳትን እንዲሁም ሃይል ሰጪ ብስኩቶች፤ 980 የውሃ መቅጃ ጄሪካኖች በድጋፍ መስጠቱን ገልጸዋል።

በተጨማሪም ተፈናቃዮቹ ለግል ንጽህና መጠበቂያ የሚውሉ 10ሺህ የሚጠጉ የልብስ ሳሙና ድጋፍ መደረጉን አስተባባሪው አመልክተዋል።

ማህበሩ በቀጣይም በደባርቅ ከተማ ውስጥ በጊዚያዊ መጠለያዎች ውስጥ ለሚገኙ ሌሎች ሶስት ሺህ ለሚደርሱ ተፈናቃይ ወገኖች ተመሳሳይ ድጋፍ ለማድረግ ዝግጅት እያካሄደ እንደሚገኝ አስታውቀዋል፡፡

የኢትዮጵያ ዜና አገልግሎት
2015
ዓ.ም