ቀጥታ፡

የኢትዮጵያ ፌደራል ፖሊስ ከፀጥታ አካላት ጋር በመሆን ስትራቴጂክ ቦታዎች አስለቀቀ

ነሐሴ 11 ቀን 2013 (ኢዜአ) አሸባሪው የህወሓት ጁንታ ትንኮሳ ያደረገባቸውን ስትራቴጂክ ቦታዎች ከፀጥታ አካላት ጋር በመሆን ማስለቀቁን የኢትዮጵያ ፌደራል ፖሊስ አስታወቀ።

አሸባሪው የህወሓት ቡድን ቆቦ ከተማን በመቆጣጠር ወደ ሌሎች የሀገራችን አካባቢዎች በቀላሉ ለማለፍ በተለምዶ የአርሴማ ተራሮች የተባሉ አራት ተራሮችን ተቆጣጥሮ ለቆቦ ከተማ ነዋሪዎች ከፍተኛ ስጋት ሆኖ ነበር።

ሆኖም የፌዴራል ፖሊስ ሰሜን ዳይሬክቶሬት ዲቪዥን አራት ፈጥኖ ደራሽ አባላት ከሀገር መከላከያ ሠራዊና ከሌሎች የፀጥታ አካላት ጋር በመቀናጀት አነስተኛ የሰው ሃይልና የነፍስ ወከፍ መሳሪያ ብቻ በመጠቀም በርካታ የጁንታውን ሃይል በመደምሰስ አራቱንም ተራሮች በአንድ ቀን በማስለቀቅ ለአካባቢው ሚሊሺያ ማስረከብ መቻላቸው ተገልጿል፡፡

የሰሜን ዳይሬክቶሬት ፈጥኖ ደራሽ ፖሊስ ሻለቃ ምክትል አዛዥ ኢ/ር ሀሰን አብዱ፤ የፌዴራል ፖሊስ አባላቱ ከሀገር መከላከያ ሰራዊትና ከሌሎች የፀጥታ አካላት ጋር በመቀናጀት አሸባሪውን የህወሓት ጁንታ ቡድን አይቀጡ ቅጣት በመቅጣት፣ የተማመነባቸውን ስትራቴጂክ ቦታዎች አስለቅቋል፡፡

የአሸባሪውን ታጣቂዎች በመደምሰስ ለአካባቢው ማህበረሰብ መረጋጋትን ፈጥረዋል፡፡አባላቱ በአሁኑ ወቅት ወደ ሌላ ግዳጅ ለመሰማራት ዝግጅታቸውን አጠናቀው ትእዛዝ እየተጠባበቁ መሆናቸውን ፌዴራል ፖሊስ አስታውቋል።


የኢትዮጵያ ዜና አገልግሎት
2015
ዓ.ም