ቀጥታ፡

ኢትዮጵያ በዓለም ወጣቶች አትሌቲክስ ሻምፒዮና 25 አትሌቶችን ታሳትፋለች

 ነሐሴ 11/2013 (ኢዜአ) በዓለም ወጣቶች አትሌቲክስ ሻምፒዮና ኢትዮጵያ 25 አትሌቶችን ታሳትፋለች።
የዓለም ከ20 ዓመት በታች የወጣቶች አትሌቲክስ ሻምፒዮና  በኬኒያ ናይሮቢ ከተማ ከነገ ጀምሮ ለአምስት ተከታታይ ቀናት ይካሄዳል።

ኢትዮጵያ በዚህ ውድድር ኢትዮጵያ 15 ሴቶችና 10 ወንዶች በድምሩ 25 አትሌቶችን ታሳትፋለች።

ለውድድሩ የኢትዮጵያ አትሌቲክስ ልዑካን ቡድን ከትናንት በስቲያ ወደ ቦታው አቅንቷል።

ልኡካኑ በስፍራው ሲደርስም በኬንያ የኢትዮጵያ አምባሳደር መለስ አለም አቀባበል አደርገዋል።

ውድድሩ በነገው እለት የሚጀመር ሲሆን ኢትዮጵያ ከ400 ሜትር ጀምሮ ባሉ ርቀቶች በስምንት የውድድር አይነቶች ትካፈላለች።

በዚህ ውድድር ከ110 አገራት የተውጣጡ 1 ሺህ አትሌቶች በተለያዩ ርቀቶች የሚፎካከሩ ይሆናል።

የኢትዮጵያ ዜና አገልግሎት
2015
ዓ.ም