በልዩ ዘመቻዎች ኃይል ማሰልጠኛ ማዕከል የመሰረታዊ ወትድርና የስልጠና መክፈቻ ስነስርዓት ተካሄደ - ኢዜአ አማርኛ
በልዩ ዘመቻዎች ኃይል ማሰልጠኛ ማዕከል የመሰረታዊ ወትድርና የስልጠና መክፈቻ ስነስርዓት ተካሄደ
ሰኔ 11 ቀን 2013 (ኢዜአ) በመከላከያ ሚኒስቴር የልዩ ዘመቻዎች ኃይል ማሰልጠኛ ማዕከል የመሰረታዊ ወትድርና የስልጠና መክፈቻ ስነ-ስርዓት ተካሄደ፡፡
የማሰልጠኛ ማዕከሉ ዋና አዛዥ ኮ/ል ዋለልኝ ታደሰ ፣ በትልቅ ሞራልና ወኔ እምቢ ለሀገሬ ብላችሁ ሀገራችሁን በቅንነትና በታማኝነት ለማገልገል ክቡር የሆነውን የውትድርና ሙያ ለመቀላቀል ከተለያዩ የሀገራችን ጫፍ በመክተታችሁ ኮርቻለሁ ብለዋል ።
ሽብርተኛውን የጁንታ ቡድን ለመደምሰስ በማሰልጠኛ ማዕከላችን የሚሰጡትን ወታደራዊ ስልጠናዎችንና ወታደራዊ ሳይንሶችን ከእውቀት ጋር በመደመር ስልጠናችሁን በተገቢው ሁኔታ በማጠናቀቅ ሀገር ከእናንተ የምትፈልገውን ሁሉ አሟልታችሁ ማገልገል ይጠበቅባችሗል ማለታቸውን መከላከያ ሚኒስቴር አስታውቋል።