ኢዜማ የኢትዮጵያን ህልውና ለማስከበር ዜጎች በጋራ እንዲቆሙ ጥሪ አቀረበ - ኢዜአ አማርኛ
ኢዜማ የኢትዮጵያን ህልውና ለማስከበር ዜጎች በጋራ እንዲቆሙ ጥሪ አቀረበ
ነሐሴ 10/2013(ኢዜአ) የኢትዮጵያን ህልውና ለማስከበር ዜጎች በጋራ እንዲቆሙ የኢትዮጵያ ዜጎች ለማኅበራዊ ፍትሕ (ኢዜማ) ጥሪ አቀረበ፡፡
ኢዜማ በወቅታዊ ሀገራዊ ጉዳይ ላይ በዛሬው እለት መግለጫ ሰጥቷል፡፡
የፓርቲው ዋና ጸኃፊ አቶ አበበ አካሉ በመግለጫቸው የኢትዮጵያን ህልውና ለማስከበር ዜጎች በጋራ እንዲቆሙ ጠይቀው ፓርቲው ለአገር ህልውና ዘመቻው አስፈላጊውን ድጋፍ ያደርጋል ብለዋል።
ኢዜማ አሸባሪው የሕወሓት ቡድን በኢትዮጵያዊያን ላይ እያደረሰ ያለውን ከፍተኛ ጉዳት እና የደቀነው የአገር ህልውና አደጋ ለመመከት ከሕዝብ እና ከመንግሥት ጎን ይቆማል ሲሉ አረጋግጠዋል።
መንግሥትም በአሸባሪው ሕወሓት እና ሸኔ ላይ የማያዳግም እርምጃ በመሰድ የኢትዮጵያን ህልውና ማስጠበቅ ይኖርበታል፤ ህዝብንም ከስጋት መታደግ አለበት ብለዋል።
አሸባሪው ህወሃት በፈጠረው ችግር ለተፈናቀሉ ወገኖች ድጋፍ የሚውል 250 ሺህ ብር ለቀይ መስቀል እንደሚያስረክብ ተገልጿል።