ከመከላከያ ሰራዊት ጎን በመሆን የአሸባሪው ህወሓትን ግብዓተ መሬት እናፋጥናለን - ኢዜአ አማርኛ
ከመከላከያ ሰራዊት ጎን በመሆን የአሸባሪው ህወሓትን ግብዓተ መሬት እናፋጥናለን
ነሃሴ 7/2013 (ኢዚአ) የአሸባሪው ህወሓት ግብዓተ መሬት እስኪረጋገጥ ድረስ ከመከላከያ ሰራዊት ጎን በመቆም ሃገራችን የምትፈልግብንን ግዴታ እንወጣለን ሲሉ ለኢዜአ የተናገሩት የሻሸመኔ ከተማ እና አከባቢዋ ነዋሪዎች ናቸው።
ነዋሪዎቹ ለኢዚአ በሰጡት አስተያየት ሉዓላዊነቷ በህዝቦችዋ ተጠብቆ የቆየች አገር በአሸባሪው ህወሓት እንደማትፈርስና ለዚህም የትኛውንም መስዋዕትነት ለመክፈል ዝግጁ ናቸው።
የሻሸመኔ ከተማ ነዋሪ ወጣት ሙርቴሳ ከማል እንዳለው ወጣቱ የነገ የአገር ተረካቢ እንደመሆኑ በአሸባሪው ህወሓት የተቃጣውን የጥፋት ሴራ በማምከን ሉዓላዊነቷ የተረጋገጠ ሀገር እንዲትቀጥል ግንባር ቀደም ሆኖ መቆም አለበት።
በሚደረገው የህልውና ዘመቻ የሚፈለግበትን ሁሉ ለማድረግ ተነሳሽነቱ እንዳለው ወጣት ሙርቴሳ ተናግሯል።
"እኛ ወጣቶች የሚነዛውን አሉባልታ ሰምተን መደናገር ሳይሆን እውነትና ሀሰቱን ለይተን ለትክክለኛው መረጃ ጆሮ መስጠትይጠበቅብናል" ብሏል።
ወ/ሮ ፋጡማ ሀጂ የሻሼመኔ ከተማ ነዋሪ ሰሆኑ ሴቶች የሀገር ሉዓላዊነት በማስጠበቅ ያላቸው ሚና የጎላ መሆኑን ገልፀው፣ እርሳቸው በበኩላቸው በስንቅ ዝግጅት ከመከላከያ ጎን መሆናቸውን ተናግረዋል።
ባላቸው አቅም ሁሉ የሀገር ሉዓላዊነትን ለማስከበር የተጀመረው ዘመቻ እንደሚያግዙም ገልፀዋል።
በሻሸመኔ ከተማ የሀገር ሽማግሌ አቶ በዳሶ ጉደታ "አሸባሪው ህወሓት ህዝብን ከህዝብ ለማጋጨት የሀሰት ወሬዎችን መንዛት ባህሪው መሆኑን ተረድተን ለአሉባልታ ወሬ ቦታ ሳንሰጥ ተነጋግረንና ተደማምጠን የአሸባሪውን ህወጣት ግብዓተ መሬት እናፋጥናለን" ብለዋል።
አክለውም ሰላማችን ተረጋግጦ የልማት ስራችንን መቀጠል ስላለበት አሸባሪውን ለመደምሰስ ባለኝ ሁሉ ድጋፍ ለማድረግ ዝግጁ ነኝ ያሉት አቶ በዳሶ፣ "አንድነታችንን አጠናክረን ይህንን የኢትዮጵያ ጠላት የሆነውን አሸባሪ ቡድን መደምሰስ አለብን" ነው ያሉት።