ቀጥታ፡

የአሸባሪው ህወሃት ሲኦል የመግባት ህልምን ለማሳካት ቆርጠን ተነስተናል

አርባምንጭ፣ ነሐሴ 08 ቀን 2013 (ኢዜአ) "የአሸባሪው ህወሃት ሲኦል የመግባት ህልምን ለማሳካት ቆርጠን ተነስተናል" ሲሉ በአርባምንጭ ከተማ የሚኖሩ የቀድሞ ሰራዊት አባላት ገለጹ።

ላለፉት 27 ዓመታት የኢትዮጵያ ህዝብ ሰቆቃ፣ መከራና ሞት ምክንያት የነበረው አሸባሪው ህወሃት፤ በአገር መከላከያ ሰራዊት ሰሜን እዝ ላይ የፈጸመው ኢ-ሰብአዊ ድርጊት የማይረሳ ጥቁር ጠባሳ መሆኑን ገልጸዋል።

ሀምሳ አለቃ በረከት በየነ እንደተናገሩት፤ ሀገሩንና ህዝቡን ለማገልገል መስዋዕትነት እየከፈለ ያለው ሰራዊት ላይ ጥቃት ያደረሰው አሸባሪው ቡድን 'ሀገር ለማፍረስ ሲኦል እንገባለን' በሚል ሰይጣናዊ አላማ ይዞ እየተንቀሳቀሰ ነው።

“የኢትዮጵያ ህዝብም ሲኦል የመግባት ህልማቸውን እንዲያሳኩ ከዳር እስከዳር ሆ ብሎ ተነስቷል” ያሉት ሀምሳ አለቃ በረከት፤ ኢትዮጵያ በህዝቧ ተጋድሎ እንደማትፈርስ አስገንዝበዋል።

አሸባሪው ህወሃት ሲኦል የመግባት ህልሙን እንዲያሳካ የኢትዮጵያ ህዝብ ከዳር እስከዳር በአንድነት መቆሙን ገልጸዋል።

ሌላው ወታደር ታከለ ምትኩ በበኩላቸው አሸባሪው ህወሀት ኢትዮጵያውያንን በማፈን፣ በማሠርና በስውር በመግደል ወንጀል ሲፈጽም መኖሩን አስታውሰው፤ ቡድኑ አገር ለማፍረስ የያዘውን አጀንዳ ለመቀልበስ መነሳታቸውን ገልጸዋል።

ሌላው አስተያየት ሰጪ ሀምሳ አለቃ በየነ ባሳ ቡድኑ ከመሠረቱ ጀምሮ ራስ ወዳድና ለህዝብ የማይበጅ ድርጅት እንደሆነ ተናግረዋል።

ቡድኑ የኢትዮጵያን ህዝብ ሀብት እንዳሻው በመዝረፍ ህዝቡ ከድህነት እንዳይወጣ ሲያደርግ መቆየቱን አስታውሰው፤ "የብሔር ብሔረሰቦችን መብት አስከብራለሁ በሚል ሽፋን የኢትዮጵያዊያን አንድነት ሲፈታተን ቆይቷል" ብለዋል።

አሸባሪው ህወሃት ሲበዘብዝውና ሲያንገላታው የቆየውን ህዝብ ዳግም ወደ መከራ ለመመለስ ጦርነት መክፈቱን ገልጸው፤ ቡድኑን በማስወገድ ኢትዮጵያ ብቻ ሳትሆን የምስራቅ አፍሪካ ቀጣና ሰላም እንዲያገኝ ማድረግ እንደሚያስፈልግ ገልጸዋል።

በመሆኑም መንግስት ባደረገው ጥሪ መሠረት አሸባሪውን ለማስወገድ በሚደረገው ዘመቻ ለመሳተፍ መዘጋጀታቸውን ጠቁመዋል።

የኢትዮጵያ ዜና አገልግሎት
2015
ዓ.ም