ቀጥታ፡

ኢትዮጵያ አሁን ያለችበትን ወቅታዊ ፈተና በድል አድራጊነት ለማለፍ ተዘጋጅተናል

አዲስ አበባ ነሃሴ 7/2013 (ኢዜአ) ኢትዮጵያ አሁን ያለችበትን ወቅታዊ ፈተና በድል አድራጊነት ለማለፍ የድርሻውን ለመወጣት ዝግጁ መሆኑን የኢትዮጵያ ዳያስፖራ ጥምረት አስታወቀ።

የኢትዮጵያ ዳያስፖራ ጥምረት በኢትዮጵያ ያለውን ወቅታዊ ሁኔታ አስመልክቶ መግለጫ ሰጥቷል።

በመግለጫውም ኢትዮጵያ አሁን ያለችበትን ወቅታዊ ፈተና በድል አድራጊነት ለማለፍ ከመንግስት ጋር በትብብር በመስራት የድርሻውን ለመወጣት ዝግጁ መሆኑን አስታውቋል።

የጥምረቱ ሊቀመንበር ሶስና ወጋየሁ ኢትዮጵያ የገጠማትን አደጋ እንድትሻገር ዳያስፖራው መንግሥትን በመደገፍ አገር ማዳን አለበት ብለዋል።

ኢትዮጵያ አሁን ከገጠማት ችግር እንዲትወጣ ከመቼውም ጊዜ በላይ አብሮነትና ትብብር ያስፈልጋልም ነው ያሉት።

በተለይም የዳያስፖራው ማህበረሰብ ከመንግሥት ጎን ሆኖ ለአገሩ ድጋፉን በማድረግ ስለ አገሩ ዘብ እንዲቆም እየተሠራ መሆኑ ተመልክቷል።

ለኢትዮጵያ ህልውና፣ ሰላምና መረጋጋት ጥምረቱ በትኩረት እየሰራ መሆኑንም ጥምረቱ በመግለጫው አመልክቷል።

የታላቁ የኢትዮጵያ ህዳሴ ግድቡን በተመለከተም ዳያስፖራው የላቀ ድጋፍ በማድረግ ላይ መሆኑን በመጥቀስ ስለ ግድቡ በተዛባ መልኩ የሚሰራጩ መረጃዎችንም እያከሸፈ ይገኛል ተብሏል።

የኢትዮጵያ ዜና አገልግሎት
2015
ዓ.ም