ቀጥታ፡

አሸባሪውን ህወሀትና ተላላኪዎቹን በተባበረ ክንድ ለመደምሰስ የቀረበው ጥሪ ወቅታዊ ነው

ፍቼ ነሐሴ ዐ6/2ዐ13(ኢዜአ) አሸባሪው ህወሀትና ተላላኪዎችን በተባበረ ክንድ ለመደምሰስ መንግስት ያወጣው መመሪያ ትክክለኛና ተገቢ ነው ይላሉ የፍቼ ከተማና አካባቢዋ ነዋሪዎችገለጹ፡፡
ነዋሪዎቹ የሀገርን አንድነትና ሉአላዊነት ለመጠበቅ ለሚከፈለው መስዋዕትነት ያልተቆጠበ ድጋፍ እንደሚያደርጉም አመልክተዋል፡፡ 

ከነዋሪዎቹ መካከል የግራር ጃርሶ ወረዳ ወጣቶች ሊግ ሰብሳቢ ወጣት አብዲ ነገሰ በሰጠው አስተያየት በመንግስት አርቆ አስተዋይነትና ትግስት የተወሰደው የተናጥል የተኩስ ማቆም እርምጃ ለአሸባሪው ሕወሃት ጁንታ ቡድን ጊዜ መግዣና ማንሰራሪያ ሊሆን አይገባም ብለዋል፡፡ 

ይኸንን አፍራሽ የህወሃት ቡድን ድርጊት ለማክሸፍና የሀገር ሉአላዊነትን ለማስከበር ትናንት የቀረበው ጥሪ ትክክለኛና ተገቢ መሆኑንም ገልፀዋል፡፡ 

በግሉም ግንባር ድረስ በመዝመት የሀገሩን አንድነትና ሉአላዊነት ለማስከበር እንደተዘጋጀ ጠቁሟል፡፡ 

እስከ አሁንም የወር ደሞዙን ከመስጠት ባሻገር የሀገር መከላከያ ሰራዊት በወጣቶች እንዲጠናከር ወጣቶችን በመመልመል፣ በማበረታታትና በማነሳሳት ድጋፍ በማድረግ ላይ እንደሚገኝ ተናግሯል። 

ሌላው አስተያየት የሰጠው የፍቼ ከተማ የጤና ባለሙያ ወጣት ደጀኔ ደሜ መንግስት አሸባሪ ህወሃትን ለአንዴና ለመጨረሻ ጊዜ በተባበረ ክንድ ለመደምሰስ ያወጣው መመሪያ በሕዝቡ የሚጠበቅና ትክክለኛ ነው ብለዋል፡፡ 

የመንግስት የተኩስ አቁም እርምጃ የትግራይ ክልል ሕዝብ የጥሞና ጊዜ አግኝቶ እርሻውን እንዲያርስና ወደ ሰላማዊ መንገድ እንዲገባ እድል የሚሰጥ ቢሆንም የጁንታው ቡድን ለዚህ በጐ እርምጃ ቦታ አለመስጠቱ የሚያሳዝን ነውም ብለዋል፡፡ 

ይኸንን የእብሪትና የማን አለብኝነት ድርጊት ባለቤትን የኢትዮጵያ ሕዝብ ለአንዴና ለመጨረሻ ጊዜ እንዲደመስሰው የወጣው መመሪያ ተገቢ መሆኑን ገልፀዋል፡፡ 

የፍቼ ከተማ አካባቢ ሚሊሻ አባል አቶ ዘመድኩን ጨቡዴ በበኩላቸው በአሸባሪው ሕወሃት ቡድን የደረሰው የሀገር መደፈርና የሰላም ማጣት ስር እንዳይሰድ መንግስት ያወጣው የመከላከልና የማጥቃት መመሪያ ትክክለኛና አስፈላጊ ነው ይላሉ፡፡ 

በግላቸውም አሁን ካደረጉት የገንዘብ ድጋፍ በተጨማሪ ግንባር ድረስ ለመዝመት ጥሪ እየጠበቁ መሆኑን ተናግረዋል፡፡ 

የመንግስት ሰራተኛ የሆኑት ወይዘሮ ኑሪያ ኡስማንም ጁንታው አንዱን ሕዝብ ከፍ ሌላውን ዝቅ በማድረግ ለ27 አመታት ኢትዮጵያን ሲበታትን ቆይቶ ስልጣን ሲያጣ ኢትዮጵያን ለማፍረስ የማይችል መሆኑን ሕዝብ ከመንግስት ጋር በመተባበር መመሪያው አስፈላጊና ጠቃሚ መሆኑን ተናግራለች፡፡ 

የግራር ጃርሶ ወረዳ የወዴሶ ቀበሌ አርሶ አደር በነበሩ ዋሴ የኢትዮጵያን ጠላት ለመደምሰስ በጋራና በአንድነት መቆም ያስፈልጋል፡፡ 

ይኸንን ለማጠናከር መንግስት ያወጣው መመሪያ ተገቢ መሆኑን ጠቁመው ሁሉም በተሰማራበት ፀጥታን በመጠበቅና የጁንታውን ተላላኪ ሸኔ ቡድን በማጋለጥ መንግስትን ሊያግዝ እንደሚገባም ተናግረዋል፡፡ 

የኢትዮጵያ ዜና አገልግሎት
2015
ዓ.ም