ቀጥታ፡

በግንባር አሸባሪውን ቡድንና የውስጥ ተላላኪዎቹን በጋራ ተከታትለን እናስወግዳለን

አዳማ ነህሴ 05/2013 (ኢዜአ) አሸባሪውን ህወሃት ለማጥፋት የቀረበውን ጥሪ ውጤታማ ለማድረግ የውስጥ ተላላኪዎችን ከመከታተል ጀምሮ አስፈላጊውን ድጋፍ እናደርጋለን ይላሉ ኢዜአ ያነጋገራቸው የአዳማ ከተማ ነዋሪዎች ተናገሩ።

መንግስት ለሀገሪቷ የፀጥታ ሃይሎች ያስተላለፈው ጥሪ ወቅቱን የጠበቀና አስፈላጊ ነው ብለዋል ነዋሪዎቹ ።

የአዳማ ከተማ ነዋሪና የቀድሞ ሠራዊት አባል አቶ ዘለቀ አንጌቦ እንደገለጹት ህወሃት የሀገርን ነቀርሳ ነው፣ ነቀርሳው ከሀገራችን ካልጠፋ የሰው ህይውት ያጠፋል አሸባሪውን ቡድን ለማጥፋት ሁሉም ብሔር ብሔረሰቦች በአንድነት መቆም አለባቸው ብለዋል።

ህፃናት ለውጊያ አይቀርቡም ደብተርና እስክሪብቶ ቀርቦላቸው ወደ ትምህርት ቤት ነው መሄድ ያለባቸው ክላሽ ከ120 ጥይትና ሬሽን በማሸከም የትግራይ ህፃናት መጫወቻ ያደረገ ሰብዓዊነት የሌለው አረመኔ ቡድን ነው ብለዋል።

ጁንታው ከገባበት የቀበሮ ጉድጓድ ገብተን አውጥተን ለመቅበር እድሜ አይገድበኝም ያሉት አቶ ዘለቀ አሁንም የጥሪ ማስተወቂያ ለማየት ነው የመጣውት የመንግስትን ጥሪ እየተጠባበኩ ነው ብለዋል።

መንግስት በውስጡ የተሰገሰጉ የውስጥ አርበኞችን ማጥራት አለበት፣ ውስጣችን ሆነው ለአሸባሪው ቡድን መረጃ በማቀበልና በገንዘብ የሚደግፉትን አሁን ማጥራት የሁሉም ሃላፊነት መሆኑን ገልጸዋል።

ሀገር ከተደፈረች በኋላ ጡረታ የለም፣ ዳቦ መቁረስ አንችልም ዳቦው ድንጋይ መሆኑን አውቀን የሀገር መመኪያና መከታ ከሆነው ሠራዊታችን ጎን ባለን አቅም ሁሉ መቆም አለብን ነው ያሉት።

መስጊድና ቤተክርስያን ውስጥ በሌሊት ጉድጓድ እያስቆፈረ ህዝቡን እያስለቀሰ የጦር መሳሪያ የሚቀብር የወንበዴ ቡድን መሆኑንም አመልክተዋል።

“የመንግስት ውሳኔ እጅግ አስፈላጊና ወቅቱን የጠበቀ ነው” ያሉት ደግሞ ሌላኛው የአዳማ ከተማ ደምበላ ክፍለ ከተማ ነዋሪ አቶ ጀማል ሁሴን ናቸው።

“ሰላም ማስጠበቅ የመንግስት ብቻ ሳይሆን የእያንዳንዳችን ጉዳይ ነው” ያሉት አቶ ሁሴን ይህችን አየር ያገኘነው ሰላም በመኖሩ ነው ብለዋል።

“ለፀጥታ ሃይሎች በመንግስት የተላለፈው መመሪያ ግቡን እንዲመታ ከመቼውም ጊዜ በላይ የአካባቢያችንንና የሀገራችንን ሰላም የመጠበቅ ግዴታ አለብን ነው” ያሉት ።

"ሁላችንም የመከላከያ ሠራዊቱን በሀብት፣ በደም ልገሳና በቦታው ድረስ በመሄድ ማገዝ አለብን፣ ከዚህም አልፈን ሁሉም ቤቱን ሰፈሩንና አካባቢው ከሰርጎ ገቦች መጠበቅ አለበት" ብለዋል።

በተለይ አመራሩ በሀገራችንና በአካባቢው የተጀመረው ማህበራዊና ኢኮኖሚያዊ ልማት ተጠናክሮ እንዲቀጥል ህዝቡን በማስተባበርና በመምራት ከጎኑ አሰልፎ 24 ሳዓት መስራት ግዴታ አለበት ብለዋል።

ህወሃት ዜጎች ተረጋግተው በሰላም እንዳይኖሩ፣ መንግስት ህዝብና ሀገርን በአግባቡ እንዳይመራ ፊቱን ወደ ልማቱ እንዳያዞር እያደረገ ያለ የጥፋት ቡድን በመሆኑ የተላለፈው ጥሪ ወቅቱን የጠበቀ መሆኑን የገለጹት ደግሞ አቶ ነጋሽ ግርማ ናቸው።

አሸባሪውን ቡድን ለማስወገድ እየተደረገ ያለው ዘመቻ ውጤታማ እንዲሆን ህብረተሰቡ ተደራጅቶ አካባቢውን እየጠበቀ መሆኑን ጠቅሰው “ፀጉረ ልውጦችን በመከታተልና ለፀጥታ አካላትን አሰልፎ በመስጠት ግዴታችንን መወጣት አለብን” ብለዋል።

"በከተማዋም ሆነ በክልሉ የተጀመረው ልማት በአፍራሽ ሃይሎች ሴራ ለአፍታም እንዳይቆምና እንዳይደናቀፍ በገንዘባችን፣ በእውቀትና በጉልበታችን በማገዝ ከዳር ማድረስ አለብን" ብለዋል።

የደምበላ ክፍለ ከተማ ነዋሪ አቶ ፋኖሴ ግርማ በበኩላቸው “ውሳኔው በሀገራችን ላይ በውስጥና በውጭ ጠላቶች የተቃጣውን ስጋት ለማስወገድ ክልላችንንና ከተማችንን ብሎም ቀበሌያችንን ጭምር እንዴት ነቅተን መጠበቅ እንዳለብን ያሳየን ነው” ብለዋል።

በተለይ ህዝቡ ችግሩን በትክክል አውቆ በተጠንቀቅ ከመንግስትና ከመከላከያ ጎን እንዲሆን በማንቃትና በማስተባበር ጭምር አካባቢውን እንዲጠብቅ አቅጣጫ የሰጠ ጥሪ መተላለፉንም አስረድተዋል።

“መንግስት የመጨረሻውን እርምጃ መውሰድ ይኖርበታል” ያሉት አቶ ፋኖሴ ህብረተሰቡ በቤተሰቡ፣ በጎረቤቱና በአካባቢው አደረጃጀቱን በማጠናከር ሰላሙን ከማስጠበቅ ባለፈ መከላከያን በሁሉም ነገር ማገዝ አለበት” ብለዋል።

የኢትዮጵያ ዜና አገልግሎት
2015
ዓ.ም