ቀጥታ፡

ኢትዮጵያ ለኬንያ ነፃነት ትልቅ አስተዋፅኦ አድርጋለች --ኬንያዊ የታሪክ ተመራማሪ

ነሀሴ 5/2013 (ኢዜአ) ለኬንያ ነፃነት ጎህ ለቀደደው የማው ማው ንቅናቄ ኢትዮጵያ ትልቅ አስተዋፅኦ እንደነበራት ኬንያዊ የታሪክ ተመራማሪ ፕሮፌሰር ማሻሪያ ሙነኔ ገለጹ።

ለኬንያ ነፃነት ጎህ ለቀደደው የማው ማው ንቅናቄ ኢትዮጵያ ትልቅ አስተዋፅኦ እንደነበራት ዕውቁ ኬንያዊ የታሪክ ተመራማሪ ፕሮፌሰር ማሻሪያ ሙነኔ የኢ.ፌ.ዲ.ረ ኤምባሲ በናይሮቢ ጉብኝት ባደረጉበት ወቅት ገልጸዋል።

የአድዋ ድል ለማው ማው አርበኞች መነቃቃት እንደፈጠረም ጠቅሰዋል።

ፕሮፌሰር ማቻሪያ በንቅናቄው ላይ ኢትዮጵያ በነበራት ጉልህ አስተዋፅኦ ላይ ተጨማሪ ጥናት አየሰሩ መሆናቸውን ጠቁመዋል።

በሁለቱ አገሮች ከቀዳማዊ ኃይለ ስላሴ እና ጆሞ ኬንያታ ጊዜ የጀመረው ወዳጅነት በመሪዎች ደረጃ የቀጠለ መሆኑን ምሁሩ ጠቁመው ፤ ሚዛናዊ የሆነ የአፍሪካ ታሪክ በአግባቡ መጻፍ እንዳለበት አስገንዝበዋል፡፡

አምባሳደር መለስ ዓለም በበኩላቸው የሁለቱ አገሮችን ጠንካራ ግንኙነት በተለያዩ መስኮች መቀጠሉን ጠቁመው ፤ የሁለቱን አገሮች ታሪክ ጥናት እና ምርምር ለማካሄድ ፕሮፌሰሩ ላሳዩት ተነሳሽነት አድናቆታቸውን ገልጸዋል፡፡

የሁሉቱን አገሮች ህዝብ ትስስር የሚያጠናክረውን የምርምር ሥራቸው ውጤታማ ይሆን ዘንድ ኤምባሲው የበኩሉን ድጋፍ እንደሚያደርግ ጠቁመዋል፡፡

ፕሮፌሰር ሙኔን በተባበሩት መንግስታት ድርጅት ውስጥ አገሮች ከቀኝ አገዛዝ ነጻ መውጣት ዙሪያ በከፍተኛ ባለሙያነት እንዲሁም በኬንያ ሰፊ ተነባብነት ባላቸው ጋዜጦች እና የተለያዩ የምርምር ጽሁፎችን በማቅረብ እንደሚታወቁ በኬንያ የኢትዮጵያ ኢምባሲ መረጃ ያሳያል፡፡

የኢትዮጵያ ዜና አገልግሎት
2015
ዓ.ም