ቀጥታ፡

የጣና በለስ ኃይል ማመንጫ ጣቢያው በበጀት ዓመቱ 3ሺህ 248 ጊጋ ዋት ሰዓት ለማመጨት ተዘጋጅቷል

ነሃሴ 03/2013 (ኢዜአ) የጣና በለስ ኃይል ማመንጫ ጣቢያው በበጀት ዓመቱ 3ሺህ 248 ጊጋዋት ሰዓት ለማመንጨት መዘጋጀቱን አስታወቀ፡፡

የጣቢያው ሥራ አስኪያጅ ቢምረው ዳኜ እንደገለጹት፤ የጣቢያው አራቱም ዩኒቶች በጥሩ ሁኔታ ላይ ስለሚገኙ በተጠናቀቀው በጀት ዓመት ከተከናወነው የሚልቅ ኃይል ለማምረት ታቅዷል፡፡

የጥገና ባለሙያዎች አቅም እያደገ መምጣቱና ከሀገር ውጪም ሆነ ከማዕከል የጥገና ባለሙያ እስኪመጣ ሳይጠበቅ የሚሰራ ባለሙያ መፈጠሩ፣ዩኒቶች በጥገና ምክንያት ከሥራ ውጪ የሚሆኑበት ጊዜ መቀነሱና የተሻለ የውሃ መጠን በክረምቱ እንደሚኖር ታሳቢ መደረጉ እቅዱን ከፍ አድርጎ ለማቀድ መነሻ ሆኗል ብለዋል፡፡

ጣና በለስ በተጠናቀቀው በጀት ዓመት 2ሺ 773 ጊጋ ዋት ኢነርጂ በማምረት የዕቅዱን 90 በመቶ ያሳካ ሲሆን በዓመቱ ከተመረተው ኢነርጂ ውስጥ ጣቢያው የ17 ነጥብ 5 በመቶ ድርሻ እንደነበረው ተገልጿል፡፡

የኢትዮጵያ ዜና አገልግሎት
2015
ዓ.ም