በአሜሪካ ዳላስ ከ140 ሺህ ዶላር በላይ በኢትዮጵያ ድጋፍ ለሚሹ ወገኖች ተሰበሰበ - ኢዜአ አማርኛ
በአሜሪካ ዳላስ ከ140 ሺህ ዶላር በላይ በኢትዮጵያ ድጋፍ ለሚሹ ወገኖች ተሰበሰበ
አዲስ አበባ፣ ነሃሴ 02/2013 (ኢዜአ) በአሜሪካ ዳላስ ከተማ በተካሄደው የአብሮነት ምሽት በኢትዮጵያ ድጋፍ ለሚሹ ወገኖች ከ140 ሺህ በላይ የአሜሪካን ዶላር ተሰበሰበ፡፡
በኢትዮጵያውያን የዳላስ አብሮነት ምሽት ስነስረአት ላይ ድንቅ የአጋርነት ትስስርና ጠቃሚ መልዕክቶችን የተላለፉ መሆኑም ተገልጻል፡፡
በስነስረአቱ ላይ በኢትዮጵያ ድጋፍ ለሚሹ ወገኖች በአንድ መድረክ ብቻ ከ140 ሺ የአሜሪካን ዶላር በላይ በማሰባሰብ አዲስ ክብረ ወሰን ሆኗል፡፡
በአሜሪካ የኢትዮጵያ አምባሳደር ፍፁም አረጋ በይፋዊ የማህበራዊ ገጻቸው ላይ እንዳሰፈሩት "ይህ ድጋፍ እንዲገኝ ላስተባበሩ ለኮሚቴው ሰብሳቢና አመራሮች፣ ለኃይማኖት አባቶች፣ ለመድረክ መሪዎች እንዲሁም በጨረታ ጭምር በተደጋጋሚ ለለገሳችሁ ሁሉ የከበረ ምስጋናችን ይድረሳችሁ" ብለዋል፡፡
በቀጣይ የዳላሶችን ፈለግ በመከተል በሌሎችም ከተሞች የተጠናከረ የአጋርነትና የልገሳ ፕሮግራም እንደሚካሄድ የሚተማመኑ መሆኑን ገልጸዋል፡፡