በኢትዮጵያ የቀድሞ ፕሬዝዳንት ዶክተር ሙላቱ ተሾመ የተቋቋመ ድርጅትን የማስተዋወቅ መርሃ ግብር እየተካሄደ ነው - ኢዜአ አማርኛ
በኢትዮጵያ የቀድሞ ፕሬዝዳንት ዶክተር ሙላቱ ተሾመ የተቋቋመ ድርጅትን የማስተዋወቅ መርሃ ግብር እየተካሄደ ነው
ሀምሌ 30/2013 (ኢዜአ) በኢትዮጵያ የቀድሞ ፕሬዝዳንት ዶክተር ሙላቱ ተሾመ የተቋቋመው "ሴንተር ፎር ኢንቨስትመንት ኔትዎርኪንግ ኢትዮጵያ" የተሰኘ ድርጅት የማሰተዋወቅ መርሃ ግብር እየተካሄደ ነው።
በቀድሞው ፕሬዚዳንት በዶክተር ሙላቱ የዲፕሎማሲ ህይወት ላይ የሚያጠነጥነውና በዓለምነህ ረጋሳ የተጻፈው "ዶክተር ሙላቱ ተሾመ ዊርቱ እና የኢትዮጵያ ዓለም አቀፍ ዲፕሎማሲ ከ1949 ዓ.ም እስከ - - - " የሚለው መጽሓፍ የምረቃ ሥነ ስርዓት እየተካሄደ ይገኛል።
በዶክተር ሙላቱ ተሾመ የተቋቋመው "ሴንተር ፎር ኢንቨስትመንት ኔትዎርኪንግ ኢትዮጵያ" የሚለው ተቋም ለትርፍ ያልተቋቋመ ሲሆን፤ በኢንቨስትመንት የግሉን ዘርፍ ከመንግስት ጋር በማገናኘት ድልድይ ሆኖ ያገለግላል።
በዚህም ከተቋሙ ኢትዮጵያ በኢንቨስትመንት ዘርፍ ለምታከናውናቸው ተግባራት የበኩሉን አስተዋጽኦ ይጠበቃል።
ድርጅቱ ከኢንቨስትመንት ኮሚሽን እና ከኢትዮጵያ የንግድና ዘርፍ ማህበራት ጋር አብሮ መስራት የሚያስችለውን ስምምነት መፈራረሙም ተገልጿል።
የኢንቨስትመንት ኮሚሽነር ለሊሴ ነሜ፤ በዚሁ ወቅት ድርጅቱ ኢንቨስትመንት ለመሳብ ፋይዳ እንዳለው ገልጸዋል።
በመርሃ ግብሩ ላይ ፕሬዝዳንት ሳህለወርቅ ዘውዴ፣ ዲፕሎማቶች እና ሚኒስትሮች ተገኝተዋል።