የደቡብ ክልል ለመከላከያ ሠራዊት በሁለተኛ ዙር ያደረገውን ከ66 ሚሊየን በላይ ብር ድጋፍ ዛሬ አስረከበ - ኢዜአ አማርኛ
የደቡብ ክልል ለመከላከያ ሠራዊት በሁለተኛ ዙር ያደረገውን ከ66 ሚሊየን በላይ ብር ድጋፍ ዛሬ አስረከበ
ሃምሌ 29/2013 (ኢዜአ) የደቡብ ብሄር ብሄረሰቦችና ህዝቦች ክልል ህዝብና መንግስት ለመከላከያ ሠራዊት በሁለተኛ ዙር ያደረገውን ከ66 ሚሊየን ብር በላይ ድጋፍ ለመከላከያ ሚኒስቴር አስረከበ።
ድጋፉንም የመከላከያ ሚኒስቴር ዴኤታ ማርታ ሉዊጂ እና የመከላከያ ሚኒስቴር የህዝብ ግንኙነት ሃላፊ ኮሎኔል ጌትነት አዳነ ተረክበዋል።ክልሉ ለሁለተኛ ዙር በዓይነትና በገንዘብ የሰበሰበውን የቁሳቁስና ገንዘብ ድጋፍ ነው በዛሬው ዕለት ያስረከበው።
ከድጋፉ ውስጥ 40 ሚሊየን 243 ሺህ በላይ በጥሬ ገንዘብ የተሰበሰበ ሲሆን 26 ሚሊየን 697 ሺህ በላይ የሚሆነው ገቢ በዓይነት በድምሩ 66 ሚሊየን 935 ሺህ ብር በላይ የሚገመት መሆኑም በርክክቡ ወቅት ተነግሯል።
በዓይነት ከተሰበሰበው ገቢ 336 ሰንጋዎች፣ 55 በጎች፣ 279 ፍየሎች እንዲሁም ሌሎች ምግብና ምግብ ነክ ቁሳቁሶች መኖራቸውም ተገልጿል።የደቡብ ክልል በአንደኛ እና በሁለተኛ ዙር 104 ሚሊየን 167 ሺህ በላይ የሚገመት ድጋፍ በዓይነትና በገንዘብ ድጋፍ ማድረጉ ተመልክቷል።
የኢትዮጵያ ህዝብ ከዳር እስከ ዳር ለመከላከያ ሠራዊቱ ድጋፍ በማድረግ ላይ መሆኑ ይታወቃል።