ከተቋቋሙለት አላማ ውጭ ሲንቀሳቀሱ የተገኙ 3 የተራድኦ ድርጅቶች ታገዱ - ኢዜአ አማርኛ
ከተቋቋሙለት አላማ ውጭ ሲንቀሳቀሱ የተገኙ 3 የተራድኦ ድርጅቶች ታገዱ
ሀምሌ 28/2013 (ኢዜአ) ከተቋቋሙለት አላማ ውጭ ሲንቀሳቀሱ የተገኙ 3 የተራድኦ ድርጅቶችን ማገዱን የሲቪል ማህበረሰብ ድርጅቶች ኤጀንሲ አስታውቋል።
የታገዱት ድርጅቶችም አንደኛ MSF HOLLAND ሁለተኛ NORWEGIAN REFUGEE COUNCIL እና ሶስተኛ AL MAKTOUME FOUNDATION የተባሉ የውጭ ድርጅቶች የኢትዬጵያ ፌደራላዊ ዲሞክራሲያዊ ሪፓብሊክ የሲቪክ ማህበራት ድርጅቶች ኤጀንሲ በሰጣቸው ፍቃድ በህጋዊነት በተለያዩ የሰብዓዊ ስራዎች ተሰማርተው እየሰሩ የቆዩ ድርጅቶች ሲሆኑ የድርጅቶቹን እንቅስቃሴ በተመለከተ ፍቃድ ሰጪው የሲቪል ማህበረሰብ ድርጅቶች ኤጀንሲ በሚያደርገው ክትትል መሰረት ድርጅቶቹ ከተቋቋሙለት አላማ ውጭ በመንቀሳቀስ ነው ተብሏል።
ከተቋቋሙበት አላማ ውጭ ሲያደርጓቸው ከነበሩ ተግባራት ውስጥም፤-
- 1ኛ- 1ኛ እና 2ኛ የተጠቀሱት ድርጅቶች የተለያዩ ሃሰተኛ መረጃዎችን በማህበራዊ ሚዲያ እና በሌሎች ዘዴዎች ሲያሰራጩ በመገኘታቸው፣
-3ኛ - ሶስቱም ድርጅቶች ስልጣን በተሰጠው አካል የስራ ፍቃድ ያልተሰጣቸውን የውጭ ዜጎችን ወደ አገር ውስጥ በማስገባት ከስድስት ወር በላይ ቀጥረው ሲያሰሩ በመገኘታቸው፤
- 3ኛ- 1ኛ የተቀመጠው ድርጅት ስልጣን በተሰጠው አካል ፍቃድ ያልተሰጣቸው የሳተላይት የሬድዬ መገናኛ መሳሪያውችን ወደ አገር ውስጥ በማስገባ የድርጂቱ ሰራተኞች አፍራሽ ለሆኑ አላማ ሲጠቀሙበት እና ይዘው ሲንቀሳቀሱ በጸጥታ አካላት ቀጥጥር ስር በመዋላቸው፣
- 4ኛ- 3ኛ የተጠቀሰው ድርጅት የትምህርት ሚንስቴር የኮቪድ-19 ፕሮቶኮልን ባለማክበር ፣ የበጀት አጠቃቀም ግልጽነት የጎደለውና በትምህርት ቤቱ ስም የሚመጣን በጀት ከአላማው ውጭ እየተጠቀመ በመሆኑ እንዲሁም በሰራተኞች አስተዳደር ችግር የታየበት በመሆኑ ምክንያት፤
ድርጅቶቹ ከተቋቋሙት አላማ ውጭና የሃርን ጥቅም በሚጻረር መልኩ ሲንቀሳቀሱ በመገኘታቸው እንዲታረሙ በተደጋጋሚ ከድርጅቶቹ ሃላፊዎች ጋር ውይይት ቢደረግም ሊያስተካክሉ ስላልቻሉ አጠቃላይ ምርመራ ተደርጎ የመጨረሻ ውሳኔ እስኪሰጥ ድረስ በአዋጅ ቁጥር 1113/2011 አንቀጽ 77(4) መሰረት አጠቃላይ የድርጅቶቹ እንቅስቃሴ ለሶስት ወራት የታገዱ መሆኑን የሲቪል ማህበረሰብ ድርጅቶች ኤጀንሲን ጠቅሶ የኢትዮጵያ ወቅታዊ ሁኔታ መረጃ ማጣሪያ አስታውቋል።