"ገድሎ አፋልጉኝ" በማለት የተካነው የህወሃት አሸባሪ ቡድን በዜጎች ሞትና ስቃይ መነገዱን ቀጥሏል - ኢዜአ አማርኛ
"ገድሎ አፋልጉኝ" በማለት የተካነው የህወሃት አሸባሪ ቡድን በዜጎች ሞትና ስቃይ መነገዱን ቀጥሏል
አዲስ አበባ፤ ሐምሌ 27 ቀን 2013 (ኢዜአ) "ገድሎ አፋልጉኝ" በማለት የተካነው የህወሃት አሸባሪ ቡድን በዜጎች ሞትና ስቃይ መነገድና የፖለቲካ ትርፍ ለማግኘት መጣሩን ቀጥሎበታል።
በኢትዮጵያ የተለያዩ አካባቢዎች የደረሱት ግጭቶችን፣ መፈናቀሎችንና ግድያዎችን በማቀናበርና በማስተባበር አሸባሪ የህወሃት ቡድን ረጃጅም እጆች እንዳሉት ይታወቃል።
ዜጎች ለዓመታት ከኖሩበትና ቤተሰብ ከመሰረቱበት ቀያቸው ሲፈናቀሉ፣ በእምነታቸውና በአመለካከታቸው ሲገደሉ ቡድኑ በቀጥታም ሆነ በተዘዋዋሪ እጁ እንዳለበት እማኞች ያረጋገጡት ጉዳይ ነው።
የጥፋት ቡድኑ ቀደም ሲል ከጅግጅጋ እስከ ወለጋ፣ በደቡብ ክልል፣ በጋምቤላ ቤኒሻንጉል ጉሙዝ፣ በአማራ እና ሌሎች ክልሎችም በርካታ ሰብዓዊና ቁሳዊ ኪሳራዎች እንዲከሰቱ አድርጓል።
አሸባሪው ህወሃት ከማዕከላዊ መንግስት ስልጣን ከወጣና ወደ ትግራይ ክልል ተጠቃሎ ከገባ በኋላ የሰሜን ዕዝ የአገር መከላከያ ሠራዊትን ከጀርባው በመውጋት አገራዊ ክህደት ፈፅሟል።
የሽብር ቡድኑ በዚህ ድርጊቱ አገርና ድንበር ጠባቂውን ሠራዊት ከመካድ አልፎ የኢትዮጵያን ሉዓላዊነት የተዳፈረ፣ በሰው ልጆች ላይ ሊፈፀም የማይችል ሰቆቃ ያደረሰ፣ ግድያና እንግልት በመፈፀምም አረመኔያዊነቱን በተግባር ያረጋገጠ ነው።
በማይካድራ ንፁሃን ዜጎች ላይ በአንድ ጀንበር የጅምላ ግድያ በመፈፀም ለሰው ልጆች የማይራራ ጨካኝና አሸባሪ ቡድን መሆኑን በተግባር አረጋግጧል።
በኢትዮጵያ የተለያዩ አካባቢዎች ዜጎችን በመግደልና በማስገደል አገር እንዲበታተን ሌት ተቀን ሲሰራ ቆይቷል።
የሽብር ቡድኑ በማይካድራ በአንድ ጀንበር በርካታ ንፁሃንን በግፍ ሲገድል ዜጎች በመሆናቸው በመላ ኢትዮጵያዊያን ላይ የከፋ የሃዘን ድባብ አሳርፏል።
የህወሃት ደጋፊዎችና አቀንቃኞች ግን የዜጎችን ሞት ሰምተው እንዳልሰሙና እንዳላዩ በማለፍ የጥፋት ቡድኑ አጋር መሆናቸውን ሲያሳዩ፤ የሰብዓዊ መብት ተቆርቋሪዎች ግን የድርጊቱን ፈፃሚዎች አውግዘዋል።
በሰዎች ላይ በተለያየ ጊዜያት የተፈፀሙትን አረመኔያዊ ድርጊቶች በማውገዝ ማዘንና ወንጀለኛውን ተጠያቂ ለማድረግ አጋዥ መሆን ሲገባቸው በዜጎች ሞት ፖለቲካዊ ትርፍ ለመግኘት ሞክረዋል።
የአሸባሪው ህወሃት የወንጀል ተግባር አሁንም ተጠናክሮ ቀጥሎ የትግራይ ህዝብ እርዳታና ድጋፍ እንዳያገኝ ከማድረግ በተጨማሪ ታዳጊ ልጆቻቸውን ከየጓዳው እየለቀመ ወደ ጦርነት በመማገድ የክፋት ጥጉን በማሳየት ላይ ነው።
በጦርነቱ የሞቱትን ወደ ተለያዩ አካባቢዎች በመውሰድ በጅምላ በመቅበር ላሰበው ቅጥፈትና የተካነበት የወንጀል ትወና ግብአት ለማድረግ እየሰራ ይገኛል።
አሸባሪው ህወሓት የቅጥፈት ፕሮፓጋንዳ ለመስራት በማቀድ “የጅምላ ጥፍጨፋ ተፈጸመ” የሚል ትርክት አዘጋጅቶ መንቀሳቀስ መጀመሩን ቀደም ብሎ መንግስት ማስታወቁ ይታወሳል።
የመረጃ ማጣሪያ ጁንታው የማይካድራ ዓይነት ጭፍጨፋ በሁመራ ከተማ ለመፈጸም ያሰበው ዕቅድ እንዳፈተለከበት ሲያውቅ የተለየ ስልት መከተሉ አሁን ይፋ ሆኗል።
ለዚህም የአሸባሪው ህወሃት ደጋፊዎችና አንዳንድ መገናኛ ብዙሃን “በሁመራ ንጹሃን ተገድለው ወንዝ ውስጥ ተጥለው” ተገኙ የሚል የተቀነባበረ የሀሰት ዘመቻ ከፍተዋል። “ገድሎ አፋልጉኝ” ማለት ይህ ነው።
በመሰረቱ አሸባሪው ህወሃት አሁን ላይ በአማራ እና አፋር ክልሎች ከከፈተው ጦርነት በተጓዳኝ ከሁመራ እስከ ማይካድራ በዜጎች ላይ የፈፀመውን ግድያና ሰቆቃ ሌላ ባለቤት ሊያበጅለት ድራማውንና ትወናውን ጀምሯል።
በሁመራ በኩል በወንዝ ዳርቻ ተገኘ ስለተባለው አስከሬንም ንፁሃንን "ገድሎ ገዳዩን አፋልጉኝ" ማለት የሚያውቅበት የህወሃት አሸባሪ ቡድን በዜጎች ሞትና ስቃይ የሚነግድ መሆኑን በግልጽ ያንጸባረቀ ነው።
የኢትዮጵያ ወቅታዊ መረጃ ማጣሪያ ቀደም ሲል ይፋ ባደረገው መረጃ የህወሃት ፕሮፓጋንዳ አራጋቢዎች የሐሰት ምስሎችን እና ስዕላዊ ቅንብሮችን በመጠቀም ሐሰተኛውን ‹የሁመራ ጭፍጨፋ› ዘመቻ እንደገና በማነሳሳት ላይ ይገኛሉ ማለቱ ይታወቃል።
የዩ ኤስ ኤ አይ ዲ ሃላፊ ሳማንታ ፓወር በሱዳንና ኢትዮጵያ ጉብኝት በሚያደርጉበት አጋጣሚ የህወሃት አሸባሪ ቡድን ቀድሞ ያሰናዳውን ይዞ "ጅራፍ ራሱ ገርፎ ራሱ ይጮሃል" እንዲሉ በተካነበት ትወና "ገድሎ እየጮኽ" ይገኛል።
የአሸባሪ ቡድኑ የወንጀል ቅንብር የዩ ኤስ ኤ አይ ዲ ሃላፊ ሳማንታ ፓወር መገኘት ጋር "ገድሎ መጮሁ" ለምን?